am_mat_text_ulb/25/14.txt

1 line
509 B
Plaintext

\v 14 ነገሩ ወደ ሌላ አገር መሄድ ያሰበ ሰውን ይመስላል፤ አገልጋዮቹን ጠርቶ በሀብት በንብረቱ ሁሉ ላይ ኀላፊነት ሰጣቸው። \v 15 እንደ ዐቅማቸው መጠን ለአንዱ አምስት ታላንት፣ ለሌላው ሁለት፣ ለሌላው ደግሞ አንድ ታላንት ሰጣቸውና ሄደ። \v 16 አምስት ታላንት የተቀበለው ወዲያውኑ ሄዶ ነገደበት፤ ሌላ አምስት አተረፈ።