am_mat_text_ulb/23/34.txt

1 line
755 B
Plaintext

\v 34 ስለዚህ ነቢያትን፣ አስተዋይ ሰዎችንና የአይሁድ ሕግ መምህራንን ወደ እናንተ እልካለሁ፡፡ አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ፣ ትሰቅላላችሁ፤ ሌሎቹን በምኵራቦቻችሁ ትገርፋላችሁ፣ ከከተማ ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፡፡ \v 35 ከጻድቁ አቤል አንሥቶ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካካል እስከ ገደላችሁት የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ደም ድረስ፣ በምድር ላይ በፈሰሰው ጻድቃን ደም ሁሉ ትጠየቃላችሁ፡፡ \v 36 እውነት ነው የሞላችሁ፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይሆናሉ፡፡