am_mat_text_ulb/21/15.txt

1 line
672 B
Plaintext

\v 15 \v 16 \v 17 15 ነገር ግን የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን እርሱ ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች ባዩና በቤተ መቅደስ ልጆች፣ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ” በማለት ሲጮኹ በሰሙ ጊዜ፣ ተቆጡ። 16 “ሕዝቡ የሚሉትን ትሰማለህን?” አሉት። ኢየሱስ፣ “አዎ! ነገር ግን ‘ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ’ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው። 17 ከዚያም ኢየሱስ ትቷቸው ከከተማው ወጣና ወደ ቢታንያ ሄደ በዚያ ዐደረ።