\c 22 \v 1 ኢየሱስም ደግሞ እንዲህ በማለት በምሳሌ መለሰላቸው፤ \v 2 "መንግሥተ ሰማይ ለልጁ ሰርግ የደገሰ አንድ ንጉሥ ትመስላለች፡፡ \v 3 ወደ ሰርጉ እንዲመጡ ወደ ጋበዛቸው ሰዎች አገልጋዮቹን ላከ፤ እነርሱ ግን መምጣት አልፈለጉም፡፡