am_mat_text_ulb/28/08.txt

1 line
486 B
Plaintext

\v 8 ሴቶቹ ፈጥነው በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር ከመቃብሩ እየሮጡ ሄዱ። \v 9 እነሆ ኢየሱስ አገኛቸውና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። ሴቶቹም እግሮቹን ይዘው ሰገዱለት። \v 10 ከዚያም ኢየሱስ፣ "አትፍሩ፤ ሄዳችሁ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ንገሩ፤ እዚያ ያዩኛል" አላቸው።