am_mat_text_ulb/27/54.txt

1 line
613 B
Plaintext

\v 54 የመቶ አለቃውና ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩ ሰዎች የምድር መናወጡንና የሆኑትን ነገሮች ሲያዩ በጣም ፈርተው፣ "በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነው" አሉ። \v 55 እርሱን ለመርዳት ከገሊላ ጀምሮ ኢየሱስን ተከትለው የነበሩ ብዙ ሴቶች በሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር። \v 56 ማርያም መግደላዊት፣ የያዕቆብና የዮሴፍ እናት ማርያም፣ እንዲሁም የዘብዲዎስ ልጆች እናት ከእነርሱ ጋር ነበሩ።