am_mat_text_ulb/27/17.txt

1 line
600 B
Plaintext

\v 17 ተሰብስበው እያለ ጲላጦስ፣ “ማንን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ፣ በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን?” አላቸው። \v 18 ምክንያቱም አሳልፈው የሰጡት በቅናት መሆኑን ያውቅ ነበር። \v 19 በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ እያለ ሚስቱ፣ “በዚያ ንጹሕ ሰው ላይ ምንም እንዳታደርግ፤ እርሱን በተመለከተ በዚህ ሌሊት በሕልሜ ብዙ መከራ ተቀብያለሁ” የሚል ቃል ላከችበት።