am_mat_text_ulb/26/17.txt

1 line
640 B
Plaintext

\v 17 በቂጣ በዓል በመጀመሪያው ግን ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ "የፋሲካን እራት እንድትበላ የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?" አሉት፡፡ \v 18 እርሱም፣ "ከተማው ውስጥ ወዳለ አንድ ሰው ሂዱና፣ 'መምህሩ "ጊዜዬ ደርሷል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን በአንተ ቤት ማክበር እፈልጋለሁ' ይልሃል በሉት' " አላቸው፡፡ \v 19 ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንደ ነገራቸው አደረጉ፤ የፋሲካንም እራት አዘጋጁለት፡