am_mat_text_ulb/25/41.txt

1 line
559 B
Plaintext

\v 41 ከዚያም በግራው ያሉትን፣ ‘እናንተ ርጉማን ከእኔ ራቁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ገሃነም እሳት ሂዱ። \v 42 ምክንያቱም ‘ተርቤ ነበር አላበላችሁኝም፤ ተጠምቼ ነበር አላጠጣችሁኝም፤ \v 43 እንግዳ ሆኜ ነበር አልተቀበላችሁኝም፤ ተራቊቼ ነበር አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜ፣ ታስሬ ነበር፣ እናንተ ግን አልተንከባከባችሁኝም’ ይላቸዋል።