am_mat_text_ulb/25/34.txt

1 line
564 B
Plaintext

\v 34 ከዚያም ንጉሡ በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፤ 'እናንተ አባቴ የባረካችሁ ኑ፤ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። \v 35 ተርቤ ነበር ምግብ ሰጣችሁኝ፤ ተጠምቼ ነበር የምጠጣው ሰጣችሁኝ፤ እንግዳ ሆኜ ነበር አስተናገዳችሁኝ፤ \v 36 ተራቊቼ ነበር አለበሳችሁኝ፤ ታምሜ ነበር ተንከባከባችሁኝ፤ ታስሬ ነበር ጠየቃችሁኝ' ይላቸዋል።