\v 31 የሰው ልጅ በክብሩ ከመላእክቱ ሁሉ ጋር ሲመጣ፣ በክብር ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል። \v 32 አሕዛብ ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛ በጎችን ከፍየሎች እንደሚለይ ሕዝቡን ይለያቸዋል። \v 33 በጎቹን በቀኙ፣ ፍየሎቹን በግራው ያደርጋቸዋል።