\v 24 ከዚያም አንድ መክሊት የተቀበለው አገልጋይ መጥቶ፣ 'ጌታ ሆይ፣ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበት የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ። \v 25 ስለዚህ ፈራሁ፤ መክሊትህን መሬት ውስጥ ቀበርሁት። መክሊትህ ይኸውልህ' አለው።