\v 43 ይህን ግን ዕወቁ፤ ሌባው በየትኛው ሰዓት እንደሚመጣ የቤቱ ባለቤት ቢያውቅ ኖሮ ይጠነቀቅ ነበር፤ ቤቱ አይዘረፍም ነበር፡፡ \v 44 የሰው ልጅ ባልጠበቃችሁት ሰዓት ስለሚመጣ እናንተም ብትሆኑ ተዘጋጅታችሁ መጠበቅ አለባችሁ፡፡