\v 34 ኢየሱስ ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው ፈሪሳውያን ሲሰሙ፣ በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ \v 35 ከእነርሱ መካከል ሕግ ዐዋቂ የሆነ አንዱ እርሱን ለመፈተን፣ \v 36 "መምህር ሆይ፣ ከሕጉ ሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ የትኛው ነው" ብሎ ጠየቀው፡፡