am_mat_text_ulb/22/08.txt

1 line
606 B
Plaintext

\v 8 ከዚያም ለአገልጋዮቹ እንዲህ አለ፤ 'ሰርጉ ተዘጋጅቶአል፤ ጥሪ የተደረገላቸው ሰዎች ግን የሚገባቸው ሆነው አልተገኙም፡፡ \v 9 ስለዚህ ወደ ዐውራ መንገድ ማቋረጫ ሄዳችሁ የምታገኙአቸውን ያህል ሰዎች ወደ ሰርጉ ግብዣ ጥሩ፡፡ \v 10 ሰዎቹም ወደ ዐውራው መንገድ ሄደው መልካምም ሆኑ መጥፎዎች ያገኙአቸውን ሁሉ አንድ ላይ ሰበሰቡ፡፡ ስለዚህ የግብዣው አዳራሽ በተጋባዦች ተሞላ፡፡