am_mat_text_ulb/21/31.txt

1 line
703 B
Plaintext

\v 31 ከሁለቱ ልጆች የአባቱን ትእዛዝ የፈጸመው የትኛው ነው? እነርሱ፣ "የመጀመሪያው” አሉ። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ቀድመዋችሁ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይገባሉ። \v 32 ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ ወደ እናንተ መጥቶ ነበርና፤ እናንተ ግን አላመናችሁትም፤ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ግን አመኑት። እናንተም ይህ ሲሆን አይታችሁ ታምኑት ዘንድ በኋላ እንኳ ንሰሐ አልገባችሁም።