am_mat_text_ulb/20/17.txt

1 line
589 B
Plaintext

\v 17 ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይወጣ ስለ ነበር፣ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ለብቻቸው ወሰደ፤ በመንገድ ላይም እንዲህ አላቸው፦ \v 18 እነሆ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለሕግ መምህራን ተላልፎ ይሰጣል። ሞትም ይፈርዱበታል፤ \v 19 እንዲዘብቱበት፣ እንዲገርፉት፣ እንዲሰቅሉትም ለአሕዛብ ይሰጡታል። ነገር ግን በሦስተኛው ቀን ይነሣል።"