\v 23 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "እውነት እላችኋለሁ፤ ለባለ ጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ከባድ ነው፡፡ \v 24 ደግሜ እላችኋለሁ፤ ለባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከመግባት፣ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል፡፡"