am_mat_text_ulb/19/10.txt

1 line
687 B
Plaintext

\v 10 ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን፣ "የባልና የሚስት ጉዳይ እንዲህ ከሆነ ማግባት ጥሩ አይደለም" አሉት፡፡ \v 11 ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፤ "እንዲቀበሉት የተፈቀደላቸው እንጂ፣ ሁሉም ሰው ይህን ትምህርት አይቀበለውም፡፡ \v 12 በተፈጥሮ ከእናታቸው ማኅፀን ስልብ ሆነው የተወለዱ አሉና፡፡ ሰዎች የሰለቧቸውም ይገኛሉ፡፡ ስለ መንግሥተ ሰማያት ሲሉም ራሳቸውን ስልብ ያደረጉ አሉ፡፡ ይህን ትምህርት መቀበል የሚችል፣ ይቀበለው፡፡››