am_mat_text_ulb/19/07.txt

1 line
633 B
Plaintext

\v 7 እነርሱ፣ "ታዲያ የፍቺ የምስክር ወረቀት ሰጥተን ከዚያ በኋላ እንድናባርራት ሙሴ ለምን አዘዘን?" አሉት፡፡ \v 8 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ "ከልባችሁ ድንዳኔ የተነሣ ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ ሙሴ ፈቀደላችሁ፤ ነገር ግን ከመጀመሪያው እንደዚያ አልነበረም፡፡ \v 9 እኔ እላችኋለሁ፣ ከዝሙት በቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ፣ ሌላይቱንም የሚያገባ ያመነዝራል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል፡፡"