am_mat_text_ulb/18/23.txt

1 line
518 B
Plaintext

\v 23 ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ከአገልጋዮቹ ጋር ሒሳብ ሊተሳሰብ የፈለገ ንጉሥን ትመስላለች፡፡ \v 24 መተሳሰቡን እንደ ጀመረ፣ የዐሥር ሺህ መክሊት ዕዳ ያለበትን አገልጋይ ወደ እርሱ አመጡ፡፡ \v 25 ነገር ግን የሚከፍልበት መንገድ ስላልነበረው፣ ጌታው ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር ያለውም ሁሉ ተሸጦ ክፍያው እንዲፈጸም አዘዘው፡፡