am_mat_text_ulb/18/18.txt

1 line
586 B
Plaintext

\v 18 እውነት እላችኋለሁ፣ በምድር የምታስሩት ነገር ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈቱትም ነገር ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል፡፡ \v 19 በተጨማሪም እላችኋለሁ፣ ከእናንተ ሁለቱ በምድር ስለሚለምኑት ስለ ማንኛውም ነገር ቢስማሙ፣ በሰማይ ያለው አባቴ ያደርግላቸዋል፡፡ \v 20 ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት ቦታ እዚያ በመካከላቸው እገኛለሁና፡፡