am_mat_text_ulb/17/05.txt

2 lines
650 B
Plaintext

\v 5 እርሱ ገና እየተናገረ እያለ፣ እነሆ፣ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፡፡ ከደመናውም፣ "በእርሱ እጅግ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት" የሚል ድምፅ ነበረ፡፡ \v 6 ደቀ መዛሙርቱ ድምፁን በሰሙ ጊዜ ፈሩ፣ በግንባራቸውም ወደቁ፡፡ \v 7 ከዚያም ኢየሱስ መጥቶ ዳሰሳቸውና፣ ‹‹ተነሡ አትፍሩ›› አላቸው፡፡
\v 8 ከዚያም እነርሱ ቀና ብለው ተመለከቱ፣ ነገር ግን ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም፡፡