am_mat_text_ulb/16/24.txt

1 line
600 B
Plaintext

\v 24 ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "ሊከተለኝ የሚፈልግ ማንም ቢኖር፣ ራሱን መካድ፣ የራሱን መስቀል መሸከምና እኔን መከተል አለበት፡፡ \v 25 ሕይወቱን ለማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣዋል፤ ስለ እኔ ሕይወቱን የሚያጣ ግን ያገኘዋል፡፡ \v 26 ሰው ሙሉውን ዓለም የራሱ ቢያደርግ ሕይወቱን ግን ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ሰው በሕይወቱ ፈንታ ምን መስጠት ይችላል?