am_mat_text_ulb/16/13.txt

1 line
646 B
Plaintext

\v 13 ኢየሱስም ወደ ቂሣርያ ፊልጶስ ክልል በመጣ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፣ "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ነው ይላሉ?" በማለት ጠየቃቸው፡፡ \v 14 እነርሱ፣ እንዲህ አሉ፤ "አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ የቀሩትም ኤርምያስ፣ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ፡፡" \v 15 "እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?" አላቸው፡፡ \v 16 ስምዖን ጴጥሮስ፣ "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" በማለት መልስ ሰጠ፡፡