am_mat_text_ulb/15/32.txt

2 lines
789 B
Plaintext

\v 32 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ "ለሕዝቡ አዝንላቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ከእኔ ጋር ሦስት ቀን ቈይተዋል፣ የሚበሉትም የላቸውም፡፡ በመንገድ ላይ ዝለው እንዳይወድቁ ሳይበሉ ዝም ብዬ አላሰናብታቸውም" አለ፡፡
\v 33 ደቀ መዛሙርቱ፣ "በዚህ በረሓ ይህን የሚያህል ብዙ ሕዝብ የሚያጠግብ እንጀራ ከየት እናገኛለን?" አሉት፡፡ \v 34 ኢየሱስ፣ "ስንት እንጀራ አላችሁ?" አላቸው፡፡ "ሰባት እንጀራና ጥቂት ትናንሽ ዐሣ አለ" አሉት፡፡ \v 35 ከዚያም ኢየሱስ ሕዝቡን መሬት ላይ እንዲቀመጡ አዘዛቸው፡፡