am_mat_text_ulb/15/29.txt

1 line
758 B
Plaintext

\v 29 ኢየሱስ ከዚያ ቦታ ወደ ገሊላ ባሕር አቅራቢያ ሄደ፡፡ ከዚያም ወደ አንድ ኮረብታ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ፡፡ \v 30 ብዙ ሕዝብም ወደ እርሱ መጡ፤ አንካሶችን፣ ዐይነ ስውሮችን፣ ዲዳዎችንና ጕንድሾችን፣ እንዲሁም ሌሎች ታመው የነበሩ ብዙዎችን ይዘው መጡ፡፡ በኢየሱስ እግር አጠገብም አስቀመጧቸው፤ እርሱም ፈወሳቸው፡፡ \v 31 ስለዚህ ሕዝቡ ዲዳዎች ሲናገሩ፣ ጕንድሾች ሲፈወሱ፣ አንካሶች ሲራመዱ፣ ዐይነ ስውሮችም ሲያዩ አይተው ተደነቁ፡፡ የእስራኤልንም አምላክ አመሰገኑ፡፡