|
\v 36 ኢየሱስ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ መጥተው ''በዕርሻው የነበረውን የእንክርዳዱን ምሳሌ አስረዳን'' አሉት።
|
|
\v 37 ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አለ፤ “መልካሙን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው።
|
|
\v 38 ዕርሻው ይህ ዓለም ነው፣ መልካሙ ዘር የመንግሥቱ ልጆች ናቸው። እንክርዳዱ የክፉው ልጆች ናቸው፤
|
|
\v 39 ዘሩን የዘራው ጠላት ዲያብሎስ ነው። መከሩ የዓለም መጨረሻ ሲሆን፣ አጫጆቹም መላእክት ናቸው። |