am_mat_text_ulb/08/30.txt

3 lines
589 B
Plaintext

\v 30 ከዚያ አካባቢ ብዙ ሳይርቅ በግጦሽ ላይ ያሉ ብዙ ዐሳማዎች ነበሩ።
\v 31 አጋንንቱም ኢየሱስን፣ ''የምታወጣን ከሆነ ወደዚያ የዐሳማዎች መንጋ ስደደን'' ብለው መለመናቸውን ቀጠሉ።
\v 32 ኢየሱስም፣ ''ሂዱ!''አላቸው። አጋንንቱም ወጥተው ዐሳማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ እነሆም፣ የዐሳማዎቹ መንጋ ሁሉ ወደ ታች ቁልቁለቱን እየተጣደፉ ወደ ባሕሩ ወርደው ውሃው ውስጥ ገብተው ጠፉ፡፡