am_mat_text_ulb/06/01.txt

1 line
532 B
Plaintext

\c 6 \v 1 ሰዎች እንዲያዩአችሁ የጽድቅ ተግባሮቻችሁን በፊታቸው ከማከናወን ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ ከሰማይ አባታችሁ ዋጋ አታገኙም፡፡ \v 2 ስለዚህ አንተ ምጽዋት ስትሰጥ ግብዞች የሰዎችን ከበሬታ ለማግኘት በምኵራቦችና በጐዳና ላይ እንደሚያደርጉት፣ በፊትህ ጥሩንባ አታስነፋ፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፣ ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡