\v 23 እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ልታቀርብ ከሆነና ወንድምህ አንዳች ነገር በአንተ ላይ እንዳለው ካስታወስህ፣ \v 24 መባህን በመሠዊያው ፊት ትተህ ሂድ፣ በቅድሚያ ከወንድምህ ጋር ታረቅ፣ ከዚያም ተመልሰህ መጥተህ መባህን አቅርብ።