am_mat_text_ulb/04/23.txt

1 line
817 B
Plaintext

\v 23 ኢየሱስ በምኵራቦቻቸው ውስጥ እያስተማረ፣ የመንግሥትን ወንጌልም እየሰበከና በሕዝቡ መካከል ያሉ በሁሉም የደዌና የበሽታ ዐይነት የሚሠቃዩትን እየፈወሰ በመላው ገሊላ ተዘዋወረ፡፡ \v 24 ስለ እርሱ በሶርያ ምድር ሁሉ ተወራ፤ ሕዝቡም የታመሙትን ሁሉ፣ በልዩ ልዩ ደዌና ሕመም የሚሠቃዩትን፣ በአጋንንት የተያዙትንና የሚጥል በሽታ ያለባቸውን፣ ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው፡፡ \v 25 ከገሊላ፣ ከዐሥሩ ከተሞች፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከይሁዳና ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት፡፡