\v 21 ኢየሱስ ከዚያ ዐለፍ እንዳለም ሁለት ሌሎች ወንድማማቾችን፣ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን አየ፤ ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በጀልባ ውስጥ መረቦቻቸውን ያበጃጁ ነበር፡፡ ኢየሱስም ጠራቸው፡፡ \v 22 ወዲያውኑ ጀልባዋንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት፡፡