am_mat_text_ulb/04/01.txt

1 line
634 B
Plaintext

\c 4 \v 1 ከዚያም በኋላ በዲያብሎስ ሊፈተን መንፈስ ኢየሱስን ወደ ምድረ በዳ መራው፡፡ \v 2 ኢየሱስ ዐርባ ቀንና ዐርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ፡፡ \v 3 ፈታኙ ወደ እርሱ መጣና፣ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ እንጀራ እንዲሆኑ እነዚህን ድንጋዮች እዘዛቸው›› አለው፡፡ \v 4 ኢየሱስ ግን መለሰና፣ ‹‹ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል" አለው፡፡