am_mat_text_ulb/03/10.txt

1 line
692 B
Plaintext

\v 10 አሁን መጥረቢያው በዛፎቹ ሥር ተቀምጦአል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል በእሳት ውስጥም ይጣላል። \v 11 እኔ ለንስሐ የማጠምቃችሁ በውሃ ነው፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቃል፤ ጫማውን መሸከምም እንኳ አይገባኝም። እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል። \v 12 ዐውድማውን ፈጽሞ ለማጥራትና ስንዴውን በጎተራ ውስጥ ለመክተት መንሹ በእጁ ነው። ገለባውን ግን ፈጽሞ በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።