am_mat_text_ulb/02/13.txt

1 line
661 B
Plaintext

\v 13 ጠበባኑ ከሄዱ በኋላ፣ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለትና፣ "ተነሥ፣ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፡፡ እኔ እስክነግርም ድረስ እዚያ ቈይ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልጋልና" አለው፡፡ \v 14 በዚያ ሌሊት ዮሴፍ ተነሣ፣ ሕፃኑንና እናቱንም ይዞ ወደ ግብፅ ሄደ፡፡ \v 15 ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ እዚያው ቈየ፡፡ በዚህም ጌታ፣ ‹‹ልጄን ከግብፅ ጠራሁት›› ብሎ በነቢዩ የተናገረው ቃል ተፈጸመ፡፡