am_mat_text_ulb/02/01.txt

1 line
554 B
Plaintext

\c 2 \v 1 በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን ኢየሱስ በቤተ ልሔም ይሁዳ ከተወለደ በኋላ፣ ጠቢባን ሰዎች ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ እንደዚህም በማለት ጠየቁ፤ \v 2 ‹‹የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ የት ነው? የእርሱን ኮከብ በምሥራቅ አየን፣ ልንሰግድለትም መጥተናል፡፡›› \v 3 ንጉሡ ሄሮድስ ይህን ሲሰማ ተረበሸ፤ መላው ኢየሩሳሌምም ከእርሱ ጋር ታወከ፡፡