Fri May 19 2017 16:25:10 GMT+0300 (E. Africa Standard Time)

This commit is contained in:
burje_duro 2017-05-19 16:25:11 +03:00
commit 4a3b0cabf9
434 changed files with 1538 additions and 2 deletions

3
01/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\c 1 \v 1 የንጉሥ ዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ ይህ ነው፡፡
\v 2 አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ወለደ፡፡ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፡፡
\v 3 ይሁዳም ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ እናታቸውም ትዕማር ነበረች፡፡ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፡፡ ኤስሮምም አራምን ወለደ፡፡

3
01/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 4 አራምም አሚናዳብን ወለደ፡፡ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፡፡ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፡፡
\v 5 ሰልሞን እና እስራኤላዊ ያልሆነች ሚስቱ ረዓብ ቦኤዝን ወለዱ፡፡ ቦኤዝም ኢዮቤድን ወለደ፡፡ የኢዮቤድም እናት ሌላይቱ እስራኤላዊት ያልሆነች ሴት ሩት ነበረች፡፡ ኢዮቤድም የንጉሥ ዳዊት አባት የሆነው እሴይን ወለደ፡፡
\v 6 እሴይም ዳዊትን ወለደ፡፡ ዳዊትም ሰሎሞንን ወለደ፡፡ የሰሎሞንም እናት ቀድሞ የኦርዮን ሚስት ነበረች፡፡

2
01/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 7 ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፡፡ ሮብዓምም ኢቢያን ወለደ፡፡ ኢቢያም አሳፍን ወለደ፡፡
\v 8 አሳፍም ኢዮሳፍጥን ወለደ፡፡ ኢዮሳፍጥም ኢዮራምን ወለደ፡፡ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፡፡

3
01/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 9 ዖዝያን ኢዮአታሞን ወለደ፡፡ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፡፡ አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ፡፡
\v 10 ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ፡፡ ምናሴም አሞንን ወለደ፡፡ አሞንም ኢዮስያስን ወለደ፡፡
\v 11 ኢዮስያስም የኢኮንያንና የወንድሞቹ አያት ነበር፡፡ እነርሱም ባቢሎናውያን እስራኤላውያንን ማርከው ወደ አገራቸው በወሰዱበት ጊዜ የኖሩ ናቸው፡፡

3
01/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 12 ባቢሎናውያን እስራኤላውያንን ማርከው ወደ ባቢሎን ከወሰዱ በኋላ፣ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፡፡ ሰላትያልም የዘሩባቤል አያት ነበር፡፡
\v 13 ዘሩባቤል አብድዩን ወለደ፡፡ አብድዩም ኤልያቄምን ወለደ፡፡
\v 14 ኤልያቄምም አዛርን ወለደ፡፡ አዛርም ሳዶቅን ወለድ፡፡ ሳዶቅም አኪምን ወለደ፡፡

3
01/15.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 15 አኪምም ኤልዩድን ወለደ፡፡ ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፡፡ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፡፡ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፡፡
\v 16 ያዕቆብም ዮሴፍን ወለደ፡፡ ዮሴፍም ኢየሱስን የወለደች የማርያም እጮኛ ነበር፡፡
\v 17 የኢየሱስን የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው አቅርቤዋለው፡- እንግዲህ ትውልዱ ከአብርሃም እስከ ንጉሥ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፣ ከዳዊት ጀምሮ እስራኤላውያን ወደ ባቢሎን ምርኮ እስከ ተወሰዱበት ጊዜ ድረስ ሌላ አሥራ አራት ትውልድ፣ እንዲሁም ከባቢሎን ምርኮ ጀምሮ ክርስቶስ እስከ ተወለደበት ጊዜ ድረስ አሥራ አራት ትውልድ ነው፡፡

2
01/18.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 18 የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ታሪክ እንዲህ ነበረ፡፡ እናቱ፣ ማሪያም ለዮሴፍ ታጭታ ነበር፣ ዳሩ ግን ባልና ሚስት ሆነው አብረው ከመኖራቸው በፊት፣ እርስዋ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ፀንሳ ተገኘች፡፡
\v 19 እጮኛዋ ዮሴፍ እግዚአብሔርን የሚታዘዝ ሰው ነበር፣ ስለዚህ ሳያገባት ሊተዋት ወሰነ፡፡ ነገር ግን በሰዎች ፊት ሊያሳፍራት አልፈለገም፡፡ በመሆኑም በስውር ሊተዋት ፈለገ፡፡

2
01/20.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 20 በዚህ አሳብ ላይ ሳለ፣ ከጌታ ዘንድ የተላከ መልአክ በሕልም ተገልጦ አስገረመው፡፡ መልአኩም እንዲህ አለው፡- “የንጉሥ የዳዊት ልጅ፣ ዮሴፍ ሆይ፣ ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ፡፡ እርሷዋ የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡
\v 21 ወንድ ልጅ ትወልዳለች፥ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው የሚያድናቸው ነውና፣ ስሙን ‘ኢየሱስ’ ትለዋለህ፡፡”

2
01/22.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 22 ይህ ሁሉ የሆነው ከረጅም ጊዜ በፊት እንዲጽፈው ጌታ ለነቢዩ ኢሳይያስ የተናገረው ነገር ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡
\v 23 ኢሳይያስም እንዲህ ሲል ጽፎአል፡- “እነሆ፣ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ እነርሱም አማኑኤል ይሉታል፥ ትርጓሜውም ‘እግዚአብሔር ከእኛ ጋር’ ማለት ነው፡፡”

2
01/24.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 24 ዮሴፍም ከዕንቅልፉም ሲነቃ፣ የእግዚአብሔር መልአክ ያዘዘውን አደረገ፡፡ ከማርያምም ጋር መኖር ጀመረ፡፡
\v 25 ዳሩ ግን የበኩር ልጅዋን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፡፡ ዮሴፍም ኢየሱስ ብሎ ጠራው፡፡

3
02/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\c 2 \v 1 ኢየሱስም በይሁዳ አውራጃ በምትገኝዋ በቤተልሔም ከተማ ታላቁ ንጉሥ ሄሮድስ ይገዛ በነበረበት ጊዜ ተወለደ፡፡ ኢየሱስ እንደ ተወለደ ብዙም ሳይቆይ፣ የሥነ ከዋክብት ተመራማሪዎች ራቅ ካለ ሥፍራ ከምሥራቅ ወደ ቤተልሔም ከተማ መጡ፡፡
\v 2 እንዲህ ሲሉም ሰዎችን ጠየቁ፡- “የእናንተው የአይሁድ ንጉሥ ይሆን ዘንድ የተወለደው ሕፃን የት ነው ያለው? እርሱ መወለዱን የሚያሳየውን ኮከብ በምሥራቅ ዐይተነዋል፥ ስለዚህም ልንሰግድለት መጥናል፡፡”
\v 3 እነዚያ ሰዎች የተናገሩትን ንጉሥ ሄሮድስ በሰማ ጊዜ፣ በጣም ደነገጠ፡፡ በኢየሩሳሌም ያሉ ሰዎችም እንዲሁ ታወኩ፡፡

3
02/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 4 ከዚያም የካህናት አለቆች እና ጸሐፍትን ሰበሰባቸውና ‘የክርስቶስን መወለድ ነቢያት በየት እንደ ተነበዩ? ሥፍራውን ጠየቃቸው፡፡
\v 5 እነርሱም፡- ‘በይሁዳ አውራጃ በምትገኘዋ በቤተ ልሐም ነው’ አሉት፡፡ ከረጅም ጊዜ በፊት ነቢዩ ሚልክያስ እንዲህ ሲል ጽፎአልና፡-
\v 6 “እናንተ በይሁዳ ምድር በምትገኘው በቤተልሔም ከተማ የምትኖሩ ሰዎች፣ ከተማችሁ በእርግጥም ልዩ ናት፥ ከከተማችሁ የሚወጣ ሰው ገዥ ይሆናልና፡፡ በእስራኤል የሚኖሩ ሕዝቤን ይመራል፡፡”

2
02/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 7 ንጉሥ ሄሮድስ የሥነ ከዋክብት ተመራማሪዎችን በስውር ጠርቶ ኮከቡ በመጀመሪያ የታየበትን ጊዜ ጠየቃቸው፡፡
\v 8 እንዲህም አላቸው “ወደ ቤተ ልሔም ሂዱና ሕፃኑ ያለበትን ሥፍራ ፈልጉ፡፡ ባገኛችሁትም ጊዜ፣ እኔ ራሴ ሄጄ እሰግድለት ዘንድ፣ መጥታችሁ አሳውቁኝ፡፡”

2
02/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 9 ሰዎቹም ወደ ቤተ ልሔም ሄዱ፡፡ በሚያስገርም መልኩም በምሥራቅ ምድር ሳሉ ዐይተውት የነበርው ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ቤት ላይ እስኪያርፍ ድረስ ይመራቸው ነበር፡፡
\v 10 ኮከቡን ባዩ ጊዜ፣ በታላቅ ሁኔታ ደስ እያላቸው ተከተሉት፡፡

2
02/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 11 ቤቱንም ባገኙት ጊዜ፣ ገቡ ደግሞም ሕፃኑንና እናቱን ማርያምን ተመለከቱ፡፡ ወድቀውም ሰገዱለት፡፡ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤም አቀረቡለት፡፡
\v 12 እግዚአብሔርም ተመልሰው ወደ ንጉሥ ሄሮድስ እንዳይሄዱ በሕልም አስጠነቀቃቸው፡፡ ስለዚህም ወደ አገራቸው ሲመለሱ በመጡበት መንገድ በመመለስ ፈንታ፣ በሌላ መንገድ ሄዱ፡፡

3
02/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 13 የሥነ ከዋክብቱ ተመራማሪዎች ቤተልሔምን ትተው ከተመለሱ በኋላ፣ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለት፡፡ እንዲህም አለው፡- “ተነሣ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፡፡ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ፥ ይገድሉት ዘንድ እንዲሹት ንጉሥ ሄሮድስ ወታደሮቹን ሊልክ ነውና፡፡”
\v 14 በዚያው ምሽት ዮሴፍ ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱን ወሰደ፥ ወደ ግብፅም ኮበለሉ፡፡
\v 15 ንጉሥ ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖሩ፥ ከዚያም እንደገና ግብፅን ለቀው ሄዱ፡፡ በዚህም መንገድ እግዚአብሔር ለነቢዩ ሆሴዕ የተናገረው ቃል ተፈጸመ፥ ይህም “እነሆ፣ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት፡፡” የሚል ነበር፡፡

1
02/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 16 ንጉሥ ሄሮድስም ከመሞቱ በፊት፣ እነዚያ ሰዎች እንደ ተሳለቁበት ተገንዝቦ በጣም ተናደደ፡፡ ኢየሱስ አሁንም በቤተልሔም አቅራቢያ እንደሚገኝ በማሰብ፣ ሄሮድስ ሁለት ዓመትና ከዚያ በታች ያሉ ወንድ ልጆችን እንዲገድሉ ወታደሮቹን ላካቸው፡፡ የሥነ ከዋክብት ተመራማሪዎቹ ኮከቡ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየበትን ቀን በነገሩት መሠረት አሰላ::

2
02/17.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 17 ሄሮድስም እንዲህ ባደረገ ጊዜ ከራማ ከተማ አቅራቢያ ስለ ቤተልሔም ከረጅም ዘመን በፊት ነቢዩ ኤርሚያስ እንዲህ ብሎ የጻፈው ተፈጸመ፡-
\v 18 “በራማ ያሉ ሴቶች አለቀሱ፥ ደግሞም ብዙ ዋይታ አሰሙ፥ የእነዚህ ሴቶች እናት የነበረችው ራሔል፣ ስለ ሞቱት ልጆቻቸው አለቀሰች፡፡ ሰዎችም ሊያጽናኑአት ሞከሩ፥ ነገር ግን ይህን ማድረግ አልቻሉም፥ ልጆቹ ሞተዋልኗ፡፡

3
02/19.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 19 ዮሴፍና ማርያም በግብፅ ምድር ሳሉ ሄሮድስ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የላከው መልአክ እንደገና ለዮሴፍ ተገለጠለት፡፡
\v 20 ዮሴፍንም እንዲህ አለው፡- “ተነሣ! ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ምድር ሂድ፥ የሕፃኑን ነፍስ የሚሹት ሰዎች ሞተዋልና፡፡”
\v 21 ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ወሰደ፣ ወደ እስራኤልም ተመልሰው መጡ፡፡

2
02/22.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 22 አርኬሌዎስ በይሁዳ አውራጃ በአባቱ በታላቁ ሄሮድስ ፈንታ ገዥ እንደሆነ በሰማ ጊዜ፣ ወደዚያ መሄድን ፈራ፡፡ እግዚአብሔርም ስለሚያደርገው ነገር በሕልም አመለከተው፡፡ ስለዚህም ዮሴፍ፣ ማርያምና ሕፃኑ ወደ ገሊላ አካባቢ ሄዱ፡፡
\v 23 በዚያ ይኖሩም ዘንድም ወደ ናዝሬትም ከተማ ሄዱ፡፡ በዚህም ከረጅም ጊዜ በፊት በነቢያት የተነገረው ነገር ተፈጸመ፡፡ ይህም፡- “ሰዎች ናዝራዊ ነው ይላሉ” የሚል ነበር፡፡

6
03/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,6 @@
\c 3 \v 1 1 ኢየሱስ ገና በናዘሬት ከተማ ሳለ፣ ሰዎች አጥማቂው የሚሉት ዮሐንስ፣ በይሁዳ ወዳለ የተገለለ ሥፍራ ሄደ፡፡ በዚያ ያሉ ሰዎችንም ሰበካቸው፡፡
\v 2 2 እንዲህም ይል ነበር፡- “ኃጢአትን መሥራት ልታቆሙ ይገባችኋል፥ እግዚአብሔር ንጉሥ መሆኑን በቅርቡ ያሳያል፥ ኃጢአትን መሥራት ካላቆማችሁ በእርሱ ዘንድ ሥፍራ አይኖራችሁም፡፡”
\v 3 3 ዮሐንስም መስበክ በጀመረ ጊዜ፣ ነቢዩ ኢሳይያስ ከብዙ ዘመን በፊት የተናገረው ነገር ተፈጸመ፡፡ ይህም
“የጌታን መንገድ አዘጋጁ፥
ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ
የሚጮኽ ሰው ድምፅ” የሚል ነበር፡፡

3
03/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 4 ዮሐንስ ከግመል ጠጕር የተሠራ ልብስ ይለብስ ነበር፡፡ ከረጅም ጊዜ በፊት ነቢዩ ኢሳይያስ እንደ ተናገረው በወገቡ ጠፍር ይታጠቅ ነበር፡፡ ምግቡም አንበጣና የበረሃ ማር ነበር፡፡
\v 5 ሲሰብክም ይሰሙ ዘንድ በኢየሩሳሌም ከተማ ያሉ ሰዎች፣ በይሁዳ አካባቢዎች የሚኖሩ ብዙ ሰዎች፣ እንዲሁም በዮርዳኖስ ወንዝ አቅራቢያ የሚኖሩ ሌሎች ብዙ ሰዎች ወደ ዮሐንስ ይመጡ ነበር፡፡
\v 6 ከሰሙትም በኋላ ኃጢአታቸውን በግለጽ ይናዘዙ ነበር፥ ደግሞም ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠመቃቸው፡፡

3
03/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 7 ዳሩ ግን ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ይጠመቁ ዘንድ ወደ እርሱ ሲመጡ በተመለከተ ጊዜ እንዲህ አላቸው፡- “እናንተ የእፉኝት ልጆች ከሚመጣው የእግዚአብሔር ፍርድ እንድታመልጡ ማን አስጠነቀቃችሁ? በውኑ ከእርሱ ማምለጥ የምትችሉ ይመስላችኋል!
\v 8 በዕውነት ኃጢአትን መሥራት ካቆማችሁ፣ እንግዲያውስ መልካም ነገሮችን አድርጉ፡፡
\v 9 እግዚአብሔር ከአብርሃም ልጆች ጋር እንደሚሆን ቃል መግባቱን አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን “የአባታችን የአብርሃም ልጆች በመሆናችን ምክንያት ኃጢአትን ብንሠራም እንኳ አይቀጣንም” ብላችሁ ለራሳችሁ አትንገሩ፡፡ “እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆችን ሊያስነሣለት ይችላል” ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡

3
03/10.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 10 ልክ ፍሬ የማያፈራን የፍሬ ዛፍ ሥር እንደሚቈርጥ ሰው፣ እግዚአብሔር ሊቀጣችሁ ዝግጁ ነው፡፡ እያንዳንዱን ዛፍ እንደዚያ ይቈርጠዋል፥ ደግሞም ወደ እሳት ይጥለዋል፡፡”
\v 11 እኔስ ለንሰሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፡፡ ነገር ግን ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ እርሱ ከእኔ በኋላ ይመጣል፡፡ እርሱ ከእኔ ይልቅ እጅግ ይበረታል፡፡ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፡፡
\v 12 መንሹን በዕጁ ይዞአል፣ ምርቱን ከግርዱ ለመለየትም ዝግጁ ነው፡፡ እህሉን ከሚወቃበት ዐውድማ ገለባውን ሁሉ ያስወግዳል፡፡ ገበሬ ስንዴን በጐተራ እንደሚከትት፣ ጻድቃንን ወደ ቤት ይወስዳቸዋል፤ ነገር ግን ገለባ እንደሚቃጠል፣ እንዲሁ ፈጽሞ በማይጠፋ እሳት ክፉዎችን ያቃጥላቸዋል፡፡

3
03/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 13 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ዮሐንስ ከነበረበት በገሊላ አከባቢ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጣ፡፡
\v 14 ኢየሱስም እንዲያጠምቀው ዮሐንስን በጠየቀው ጊዜ፣ ዮሐንስ እምቢ አለ፤ “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል! ይሁንና አንተ ኃጢአተኛ አይደለህም፥ ስለምንስ ልትጠመቅ ወደ እኔ መጣህ?” አለው፡፡
\v 15 ነገር ግን ኢየሱስ እንዲህ አለው፡- “እንግዲህ አሁን አጥምቀኝ፥ በዚህ መንገድም እግዚአብሔር የሚፈልግብንን ሁሉ እኛ ሁለታችን ልንደርግ ይገባናልና፡፡” በዚያን ጊዜ ዮሐንስ ሊያጠምቀው ተስማማ፡፡

2
03/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 16 ወዲያውም ኢየሱስ ከውኃ ወጣ፡፡ ከዚያም ሰማያት ተከፈቱ፥ ኢየሱስም የእግዚአብሔር መንፈስ በእርግብ አምሳል ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲቀመጥ ተመለከተ፡፡
\v 17 እግዚአብሔርም ከሰማይ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- “እነሆ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወድው ልጅ እርሱ ነው! እርሱን ስሙት!“

4
04/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,4 @@
\c 4 \v 1 ከዚያም በኋላ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ወደ ምድረ በዳ መራው፡፡
\v 2 ለአርባ ቀን እና ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ፡፡
\v 3 ፈታኙ ሰይጣንም ወደ እርሱ ቀርቦ እንዲህ አለው፣ “አንተ በዕውነት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ እነዚህን ድንጋዮች ለራስህ ዳቦ እንዲሆኑልህ ተናገር!”
\v 4 ነገር ግን ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “በጭራሽ፣ ይህን አላደርግም፣ እግዚአብሔር በቅዱሳት መጻሕፍት እንዲህ ብሎአልና፡- ‹ሰዎች በዕውነት እንዲኖሩ ካስፈለገ፣ ከምግብ ያለፈ ነገር ማግኘት ይኖርባቸዋል፤ እግዚአብሔር የተናገራቸው ቃሎቹን ማድመጥ ይኖርባቸዋል!›”

5
04/05.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,5 @@
\v 5 ቀጥሎም ዲያብሎስ ለእግዚአብሔር ቅድስት ወደ ሆነች ከተማ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ኢየሱስን ወሰዶ በመቅደሱ ከፍታ ጫፍ ላይ አቆመውና
\v 6 እንዲህ አለው፡- “አንተ በዕውነት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ ራስህን ወደ መሬት ወርውር፡፡ በእርግጥም አትጐዳም፣ እግዚአብሔር በቅዱሳት መጻሕፍት እንዲህ ብሎአልና፡-
‹ይጠብቁህ ዘንድ እግዚአብሔር መላእክቱን ያዝዛል፡፡
በምትወድቅበት ጊዜም በዕጆቻቸውም ወደ ላይ ይነሡሃል፡፡
ደግሞም እግሮችህን ድንጋይ እንዳይመታው ይጠብቁሃል፡፡›”

3
04/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 7 ኢየሱስም እንዲህ በማለት መለሰለት፡- “በጭራሽ፣ ራሴን ወደ ታች አልወረውርም፣ እግዚአብሔር እንዲሁ በቅዱሳት መጻሕፍት፡- ‹አምላክህን እግዚአብሔር ለመፈተን አትሞክር! ብሎአልና፡፡”
\v 8 እንደ ገናም ዲያብሎስ ኢየሱስን ከፍ ወዳለ ተራራ ወሰደው፡፡ በዚያም የዓለም መንግሥታትና የነበራቸውን ክብር ሁሉ አሳየውና፡-
\v 9 “ወድቀህ ብትሰግድልኝ ትገዛቸው ዘንድ እነዚህን መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም ጭምር እሰጥሃለው!” አለው፡፡

2
04/10.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 10 ዳሩ ግን ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰለት፡- “ሂድ! አንተ ሰይጣን! እኔ አልሰግድልህም፡፡ እግዚአብሔር በቅዱሳት መጻሕፍት፡- ‹ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ስገድ! እርሱንም ብቻ አምልክ! ብሎአልና፡፡”
\v 11 ያን ጊዜ ዲያብሎስ ሥፍራውን ለቆ ሄደ፥ በዚያው ቅጽበትም መላእክት ወደ ኢየሱስ መጥተው አገለገሉት፡፡

2
04/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 12 ኢየሱስ በይሁዳ ግዛት ሳለ፣ የመጥመቁ ዮሐንስ ደቀ መዘሙርት ወደ እርሱ መጥተው ንጉሥ ሄድሮስ ዮሐንስን ወኅኒ እንዳገባው ነገሩት፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ በገሊላ አውራጃ ወዳለችው ወደ ናዝሬት ከተማ ተመለሰ፡፡
\v 13 በዚያም ይኖር ዘንድ ናዝሬትን ትቶ ወደ ቅፍርናሆም ከተማ ሄደ፡፡ ቅፍርናሆም ቀድሞ የዛብሎንና ንፍታሌም ነገዶች የነበረች ከገሊላ ባሕር አጠገብ የምትገኝ ከተማ ናት፡፡

5
04/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,5 @@
\v 14 ወደዚያም የሄደው ከብዙ ዓመታት በፊት በነቢዩ ኢሳይያስ የተነገረ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው፡-
\v 15 “የዛብሎንና የንፍታሌም ምድር፣
በዮርዳኖስ ምሥራቅ ያለ የባሕር መንገድ፥
የአሕዛብ መኖሪያ የሆኑ ምድሮች፡፡”
\v 16 እነዚህ ሕዝቦች በጨለማ ያሉ ያህል እግዚአብሔርን አያውቁም፥ ዳሩ ግን የደመቀ ብርሃን የወጣላቸው ያህል፣ ዕውነትን የሚያውቁ ይሆናሉ፡፡ አዎን በሞት ፍርሃት ውስጠ ነበሩ፥ ዳሩ ግን ብሩህ የሆነ ብርሃን በላያቸው ወጣ!

1
04/17.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 17 ኢየሱስ በቅፍርናሆም ከተማ ሳለ፣ “እግዚአብሔር በንጉሥነቱ ይገለጣል፣ በሚገዛም ወቅት ይፈርድባቸኋል፡፡ ስለዚህም ከኃጢአታችሁ ተመለሱ!” እያለ መስበክ ጀመረ፡፡

3
04/18.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 18 ኢየሱስ በገሊላ ባሕር ዳር ሲጓዝ ሳለ ሁለት ሰዎችን ተመለከተ፤ አንደኛው ኋላ ላይ ጴጥሮስ በመባል የተጠራው ስምዖን ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ታናሽ ወንድሙ እንድሪያስ ነበር፡፡ የሚተዳደሩት ዓሣ በማጥመድና በመሸጥ ስለ ነበር መረባቸውን ወደ ውኃው እየጣሉ ነበር፡፡
\v 19 ኢየሱስም፣ “ከእኔ ጋር ኑና ደቀ መዛሙርቴ እንዲሆኑ ሰዎችን እንዴት እንደምታጠምዱ አስተምራችኋለሁ” አላቸው፡፡
\v 20 ወዲያውም ሥራቸውን ትተው ከእርሱ ጋር ሄዱ፡፡

2
04/21.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 21 ሦስቱም በመጓዝ ላይ ሳሉ፣ ኢየሱስ ሌሎች ሁለት ሰዎችን ተመለከተ፣ እነርሱም ያዕቆብና ታናሽ ወንድሙ ዮሐንስ ነበሩ፡፡ ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳቸው ውስጥ ሆነው መረባቸውን ይጠግኑ ነበር፡፡ ኢየሱስም ተግባራቸውን ሊተውና ከእርሱ ጋር ሊሄዱ እንደሚገባ ነገራቸው፡፡
\v 22 ወዲያውም መረባቸውንና አባታቸውን ትተው ከኢየሱስ ጋር ሄዱ፡፡

3
04/23.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 23 ኢየሱስም እነዚህን አራት ሰዎች በገሊላ አውራጃዎች ሁሉ ይወስዳቸው ነበር፡፡ ሰዎችንም በምኵራቦች ያስተምር ነበር፡፡ የእግዚአብሔር መንግሥትም እንደሚገለጥ በማሳሰብ ወንጌልን ይሰብክ ነበር፡፡ የታመው ሰዎችንም ይፈውስ ነበር፡፡
\v 24 በሌሎች የሶርያ አውራጃዎች የሚኖሩ ሰዎች ያደረጋቸውን ነገሮች በሰሙ ጊዜ በደዌ፣ በብዙ በሽታዎች፣ በጠና ደዌ የሚሠቃዩ ሰዎችን፣ በአጋንንት የተያዙ ሰዎችን፣ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፡፡ ኢየሱስም እነዚህን ፈወሳቸው፡፡
\v 25 ከዚያም ብዙ ሰዎች ተከተሉት፡፡ እነዚህም ሰዎች ከገሊላ ከአሥሩ ከተማዎች፣ ከኢየሩሳሌም ከተማ፣ እንዲሁም ከሌሎች የይሁዳ ግዛቶችና ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅ ካሉ አካባቢዎች የመጡ ነበሩ፡፡

4
05/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,4 @@
\c 5 \v 1 ኢየሱስ የተሰበሰቡትን ሰዎች ባየ ጊዜ ወደ ተራራ ወጣና ተከታዮቹን ለማስተማር ተቀመጠ፡፡ ይሰሙትም ዘንድ ወደ እርሱ ቀረቡ፡፡
\v 2 ከዚያም እንዲህ ሲል ያስተምራቸው ጀመር፣
\v 3 ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና፡፡
\v 4 በዚህ ኃጢአትን በተሞላ ዓለም የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መጽናናትን ያገኛሉና፡፡

4
05/05.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,4 @@
\v 5 የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔር የሚሠራትን አዲስ ምድር ይወርሳሉና፡፡
\v 6 በጽድቅ መኖርን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ የጽድቅን ኑሮ ይጠግባሉና፡፡
\v 7 የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና፡፡
\v 8 እግዚአብሔርን የሚያስደስቱ ብፁዓን ናቸው፥ እርሱ ባለበት ይሆናሉና፡፡

2
05/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 9 የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና፡፡
\v 10 ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና፡፡

2
05/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 11 ሲነቅፉአችሁ ሲያሳድዱአሁ በእኔም በማመናችሁ ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ፡፡
\v 12 ይህ በሚከሰትበት ጊዜ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፥ እግዚአብሔር ስለ እናንተ መልካም ያስባልና፡፡ ከእናንተ በፊት የነበሩት ነቢያትንም እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና፡፡

2
05/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 13 እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፥ ጨው ያለውን ጣዕም ቢያጣ ማንም መልካም ሊያደርገው አይችልም፡፡ ሰዎች ይጥሉትና የሚረገጥ ይሆናል፡፡
\v 14 እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፡፡ በተራራ ላይ ያለችን ከተማ ለሁሉ እንደምትታይ ሁሉ፣ ሰዎች ሁሉ እናንተን ያያሉ፡፡

2
05/15.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 15 ሰዎች መብራት ካበሩ በኋላ ከዕንቅብ በታች አያደርጉትም፥ በቤት ላሉ ሁሉ እንዲበራላቸው በመቅረዝ ላይ ያኖሩታል፡፡
\v 16 ሰዎች ሥራችሁን ያዩት ዘንድ መልካሙን ሥራችሁን እንዲህ ባለ መልኩ አድርጉት፡፡ ባዩትም ጊዜ በሰማያት ያለው አባታችሁን ያመሰግናሉ፡፡

2
05/17.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 17 “እኔ የሙሴ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ እንዳይመስላችሁ፥ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁምና፡፡”
\v 18 ዕውነት ዕውነት እላችኋለሁ ሰማይና ምድር እስኪያልፉ ድረስ፣ ይፈጸማሉ ሲል እግዚአብሔር ለጸሐፊዎቹ የተናገራቸው ነገሮች ሁሉ ዕውን እስኪሆኑ ድረስ በሕጉ ያለ ነገር ሁሉ አንዲት ነጥብ እንኳ ሳትቀር ይፈጽማሉ፡፡

2
05/19.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 19 ይህም ዕውነት ስለሆነ ከእነዚያ ትእዛዛት ትንሿን እንኳ ብትተላለፍ፣ ሌሎችም እንዲተላለፉ ብታስተምር በመንግሥተ ሰማያት ታናሽ ትሆናለህ፡፡ እነዚያን ትእዛዛት ሁሉ ብትጠብቅ፣ ሌሎችም እንዲጠብቋቸው ብታስተምር በዚያን ጊዜ ታላቅ ትሆናለህ፡፡
\v 20 ስለዚህ ምክንያት እነዚያን ሕጎች ከፈሪሳውያን እና ከጻሐፍት ይልቅ መጠበቅ ይገባችኋል ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡ ያለዚያ ከቶ መንግሥተ ሰማያት አትገቡም፡፡

2
05/21.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 21 ሌሎች “አባቶቻችን ‘አትግደል! እንዳሉ ሰምታችኋል፤ ብትገድል ግን የሸንጎ አባላት የሞት ፍርድ ያስተላልፉብሃል፡፡
\v 22 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በወንድሙ ላይ በሚቈጣ እግዚአብሔር ይፈርድበታል፡፡ ወንድምህን ደደብ ብትለው የሸንጎ ፍርድ ይገባሃል፡፡ ወንድምህን ቂል ብትለው፣ እግዚአብሔር በገሃነም ባለው እሳት ውስጥ ይጥልሃል፡፡

2
05/23.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 23 እንግዲህ መባህን በመሠዊያህ ላይ ብታቀርብ፣ በዚያም ወንድምህን ማናደድህ ትዝ ቢልህ
\v 24 መባውን በመሠዊያው ላይ ትተህ፣ ወዳናደድኸው ሰው ሂድ፡፡ ለዚያም ሰው ባደረግኸው ነገር መጸጸትህን ንገረውና ይቅር እንዲልህ ጠይቀው፡፡ ከዚያም መባህን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ሂድ፡፡

2
05/25.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 25 ስለ ጥፋትህ የከሰሰህ ባላጋራህ እንዳያስፈርድብህ፣ ዳኛውም ጥፋተኛ ብሎ እንዳይፈርድብህ ወደ ወኅኒም እንዳትገባ ገና ወደ ችሎት በመሄድ ላይ ሳላችሁ፣ ከባላጋራህ ጋር በፍጥነት ተስማማ፡፡
\v 26 ዳኛው የወሰነብህን ቅጣት ሁሉ እስክትከፍል ድረስ ከዚያ ከቶ አትወጣም፡፡ እንግዲህ ከወንድሞችህ ጋር በሰላም መኖር እንዳለብህ አስታውስ፡፡”

2
05/27.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 27 “ለአባቶቻችን እግዚአብሔር ‘አታመንዝር! እንዳለ ሰምተሃል፡፡
\v 28 እኔ ግን እላችኋለሁ ሰው ወደ ሴት ተመልክቶ በልቡ ቢመኛት፣ በልቡ እንዳመነዘረ አድርጎ እግዚአብሔር ይቈጥርበታል፡፡

2
05/29.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 29 ነገሮችን በመመልከት በኃጢአት የምትሰናከል ከሆነ፣ እነዚያን ነገሮች መመልከት አቁም፡፡ ኃጢአትህን ለማቆም ሁለቱን ዐይኖችህን የሚያስከፍል ከሆነ አድርገው፡፡ ዐይኖችህ እያዩ ወደ ገሃነም ከሚጥልህ ይልቅ ዕውር ሆነህ ኃጢአትን ማቆሙ ለእግዚአብሔር ይሻለዋል፡፡
\v 30 ዕጅህ ኃጢአት የሚያሠራህ ከሆነ፣ እርሱን መጥቀሙን አቁም፡፡ ኃጢአትን ለማስወገድ ሁለት ዕጆችህን ቈርጠህ መጣል የሚያስፈልግህ ቢሆን እንኳ፣ አድርገው፡፡ ሙሉ ሰውነትህን ይዘህ ገሃነም ከሚጥልህ ይልቅ ጉንድሽ ሆነህ ኃጢአት ማቆምህ ለእግዚአብሔር ይሻለዋል፡፡

2
05/31.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 31 እግዚአብሔር በቅዱሳት መጻሕፍት “ሰው ሚስቱን ቢፈታት፣ የፍቺዋን ጽሕፈት ይስጣት” አለ፡፡
\v 32 እኔ ግን እላችኋለሁ፡- “ሰው ዝሙት ከፈጸመች ብቻ ሚስቱን ሊፈታት ይችላል፡፡ በሌላ ምክንያት ሚስቱን ከፈታት፣ እርሷም ሌላ ሰው የምታገባ ከሆነ አመንዝራ ትሆናለች፡፡ እርሷንም የሚያገባት ሰው ምንዝርናን ይፈጽማል፡፡”

3
05/33.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 33 “የሃይማኖት መምህራን ለአባቶቻችሁ፣ “አደርገዋለሁ ብለው በእግዚአብሔር የማልኸውን ነገር አድርገው” ብለው መናገራቸውን ሰምታችኋል፡፡
\v 34 እኔ ግን እላችኋለሁ “አደርጋለሁ ብለህ ቃል በመግባት ከአንተ በሚበልጥ አትማል፡፡ በሰማይ ባለ አካል ምለህ አንድን ነገር አደርጋለው አትበል፥ እግዚአብሔር በሰማይ ዙፋኑ ተቀምጧልና፡፡
\v 35 አንድን ነገር አደርጋለሁ ብለህ በምድር አትማል፥ ምድር የእግሩ መረገጫ ናትና፡፡ አንድን ነገር አደርጋለሁ ብለህ በኢየሩሳሌም አትማል፥ ኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ከተማ ናትና፡፡

2
05/36.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 36 አንድን ነገር አደርጋለሁ፣ ያለዚያ አንገቴን ቊረጡ ብለህ አትማል፥ የአንዲቱን ጠጒርህን ቀለም መለወጥ እንኳ አትችልምና፡፡
\v 37 አንድን ነገር ለማድረግ እንዲህ የምትናገር ከሆነ፣ በዚህ መልኩ እንድትናገር ያደረገህ ሰይጣን ነው፡፡

2
05/38.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 38 እግዚአብሔር ለአባቶቻችን፣ “የጐዳችሁን ሰው ጥፋት ዐይንን በዐይን፣ ጥርስን በጥርስ መልሱ” እንዳላቸው ሰምታችኋል፡፡
\v 39 እኔ ግን እላችኋለሁ፡- “ጒዳት ያደረሰባችሁን ሰው ከመበቀል ራቁ፣ ልታስቆሙት እንኳ አትሞክሩ፡፡ በዚህ ፈንታ አንዱን ጉንጭህን ለሚመታህ፣ ሁለተኛውን አዙርለት፡፡

3
05/40.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 40 ዕጀ ጠባብህን ሊወስድ ለሚከስህ ሰው እርሱንና ይበልጥ የሚጠቅምህን ጭምር ተውለት፤
\v 41 ሮማዊ ወታደር እንድትሸከምለት አንድ ማይል ቢያስገድድህ፣ ለሁለት ማይል ተሸክመህለት ሂድ፡፡
\v 42 እንድትሰጠው የሚጠይቅህን ነገር ለጠያቂው ስጠው፡፡ ብድር ለሚጠይቅህ ብድር ስጠው፡፡”

3
05/43.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 43 እግዚአብሔር ለአባቶቻችን፣ “እስራኤላዊ ወንድምህን ውደድ፣ ባዕዳንን ደግሞ ጥላ፣ ጠላቶችህ ናቸውና፡፡” እንዳላቸው ሰምተሃልና፡፡
\v 44 እኔ ግን እላችኋለሁ፡- “ወዳጆቻችሁንም ሆነ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፡፡
\v 45 በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንድትመስሉ ይህን አድርጉ፡፡ እርሱ ለሰዎች ሁሉ በጎ ያደርጋልና፡፡ ፀሐይን በዕኩልነት ለክፉዎችም ሆነ ለጻድቃን ያወጣል፤ ሕጉን ለሚታዘዙም ሆነ ለማይታዘዙ ሰዎች በዕኩልነት ዝናብን ያዘንባልና፡፡

3
05/46.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 46 የሚወዱህን ብቻ ብትወድ፣ ከቶውንም ብድራትን ከእግዚአብሔር ዘንድ አትጠብቅ! እንደ ቀራጮች ያሉ ክፉ አድራጊ ሰዎች እንኳ፣ የሚወዷቸውን ይወዳሉና፡፡ ከእነርሱ የተሻለ ልታደርግ ይገባል!
\v 47 አዎን ወዳጆቻችሁን ብቻ ሰላም ብትሉና እነርሱን እንዲባርካቸው እግዚአብሔርን ብትጠይቁ፣ ከሌሎች ሰዎች የተለየ ነገር እያደረጋችሁ አይደላችሁም፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግ የማይታዘዙ አሕዛብ እንኳ ይህንኑ ያደርጋሉና!
\v 48 እንግዲህ እናንተ ፍጹም ታማኝ እንደ ሆናችሁ ሁሉ፣ በሰማይ ላለ አባታችሁ ፍጹም ታማኝ ሁኑ፡፡”

2
06/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\c 6 \v 1 “መልካም ስታደርጉ ሰዎች እያዩዋችሁ አለመሆኑን አረጋግጡ፡፡ እንዲያዩዋችሁና እንዲያመሰግኑዋችሁ አታድርጉ፡፡ ሰዎች ዐይተው እንዲያመሰግኑዋችሁ መልካምን የምታደርጉ ከሆናችሁ፣ በሰማያት ያለው አባታችሁ ምንም ዋጋ አይሰጣችሁምና፡፡”
\v 2 እንዲሁ ለድሆች ምጽዋት ስትሰጡ ሌሎች ጥሩምባ እንዲነፋላቸው እንደሚያደርጉ ባለ መልኩ አታድርጉት፡፡ ይህም ሰዎች ያመሰግኑዋቸው ዘንድ እነዚያ ግብዞች በምኲራቦችና በየዋና ዋና ጎዳናዎች የሚያደርጉት ነው፡፡ ሰዎች እነዚያን ግብዞች የሚያመሰግኑዋቸው መሆኑን፣ ነገር ግን ግብዞች የሚቀበሉት ብቸኛው ሽልማት ይህ እንደሆነ ብቻ ልብ በሉ!

2
06/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 3 ፈንታ ለድሆች ምጽዋት ስትሰጥ፣ የምታደርገውን ነገር ሰዎች እንዲያውቁ አታድርግ፡፡
\v 4 በዚህም መንገድ ምጽዋትህን ለድሆች ትሰጣለህ፡፡ ማንም ሳያይህ ያደርግኸውን በስውር የሚያይ አባትህ በስውር ብድራትህን ይከፍልሃል፡፡

3
06/05.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 5 “ስትጸልዩ ግብዞች የሚያደርጉትን አታድርጉ፡፡ በምኲራቦችና በዋና ዋና ጎዳናዎች ጥግ መቆምን ይወዳሉ፥ ሰዎች ዐይተው እንዲያመሰግኑዋቸው ይሻሉና፡፡ ከዚህም ሰዎች የሚያመሰግኑዋቸው መሆኑን፣ ነገር ግን የሚቀበሉት ሽልማት ይኸው ብቻ እንደሆነ ልብ በሉ፡፡”
\v 6 ዳሩ ግን እናንት ወደ ክፍላችሁ ግቡና በሩን ዘግታችሁ ማንም ሳያይ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ፡፡ ማንም በማያይበት ሥፍራ እርሱ ያያችኋል፥ ዋጋችሁንም ይሰጣችኋል፡፡
\v 7 ስትጸልዩ እግዚአብሔርን የማያውቁ ሰዎች ሲጸልዩ እንደሚያደርጉት ቃላትን ለብዙ ጊዜ አትደጋግሙ፡፡ እነርሱ ብዙ ቃላትን የተጠቀሙ ከሆኑ አማልክቶቻቸው የሚያደምጧቸውና የጠየቁትን ነገር የሚሰጡዋቸው ይመስላቸዋልና፡፡

5
06/08.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,5 @@
\v 8 እነርሱ እንደሚያደርጉት ቃላትን አትድገሙ፥ አባታችሁ እግዚአብሔር ከመጸለያችሁ በፊት የሚያስፈልጋችሁን ነገር ያውቃልና፡፡
\v 9 ስለዚህም እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፡-
“አባታችን ሆይ፥ በሰማያት የምትኖር
\v 10 ስምህ ይቀደስ፥ መንግሥትህ ትምጣ
ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች፣ እንዲሁ በምድርም ትሁን፥

8
06/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
\v 11 የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ፥
\v 12 በደላችንንም ይቅር በለን፥
እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል፣
\v 13 ወደ ፈተናም አታግባን፥
ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ፥
መንግሥት ያንተ ናትና
ኃይል ምስጋና ክብርም
ለዘላለሙ አሜን፡፡”

2
06/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 14 የሚበድሉዋችሁን ይቅር በሉ፥ ይህን የምታደርጉ ከሆናችሁ በሰማይ ያለው አባታችሁ በደላችሁን ይቅር ይላችኋል፡፡
\v 15 እናንተ ግን የሰዎችን ኃጢአት ይቅር ባትሉ፣ እግዚአብሔርም እንዲሁ በደላችሁን ይቅር አይላችሁም፡፡

3
06/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 16 ስትጾሙ ግብዞች እንደሚያደርጉት ኃዘንተኞች መስላችሁ አትታዩ፡፡ ጾመኞች መሆናቸውን ዐውቀው ሰዎች ያከብሯቸው ዘንድ ፊቶቻቸውን ያጠወልጋሉ፡፡ እነዚህን ሰዎች ሌሎች በጣም ያከብሯቸው ይሆናል፥ ዳሩ ግን እነዚህ ሰዎች የሚያገኙት ብቸኛ ዋጋ ይህ እንደ ሆነ ልብ በሉ፡፡
\v 17 እናንተ ግን ስትጾሙ እንደ ተለመደው ጠጒራችሁን ተቀቡ፥ ፊታችሁን ታጠቡ፡፡
\v 18 ይህም ሰዎች እየጾማችሁ መሆኑን እንዳይረዱ ያደርጋል፡፡ ዳሩ ግን ማንም ያላየውን የሚያይ አባታችሁ ጾማችሁን ይመለከታል፡፡ ማንም ያላያችሁ ቢሆን እንኳ እርሱ ዐይቷችኋል፥ ደግሞም እርሱ ብድራታችሁን ይከፍላል፡፡

3
06/19.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 19 በዚህ ምድር በስግብግብነት ለራሳችሁ ብዙ ገንዘብንና ቊሳቊስን አታከማቹ፥ ምድርን ሁሉ የምታጠፋ ናትና፡፡ ብልና ዝገት ብዙ ነገሮችንን ያበላሻሉ፥ ሌቦችም ይሰርቃሉ፡፡
\v 20 በዚህ ፈንታ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙ ነገሮች አድርጉ፡፡ መልካም ነገሮች ብታደርጉ፥ በሰማያት መዝገብን ለራሳችሁ ታኖራላችሁ፡፡ በሰማይ የሚጠፋ ነገር የለምና፡፡
\v 21 የከበረ መዝገብ እንደሆነ በምትቈጥሩት ነገር ላይ ልባችሁ በዚያ እንደሚሆን አስታውሱ፡፡

3
06/22.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 22 “የሰውነት መብራት ዐይን ናት፥ ነገሮችን የምታዩት በእርሱ ነውና፡፡ ነገሮችን እግዚአብሔር በሚያይበት መንገድ የምታዩ ከሆናችሁ፣ መላው ሰውነታችሁ በብርሃን እንደ ተሞላ ያህል ነው፡፡
\v 23 ዐይኖቻችን ታማሚ ከሆኑ ነገሮችን አጥርታችሁ ማየት አትችሉም፡፡ ዐይኖቻችሁ ነገሮችን አጥርታችሁ እንድታዩ አያስችላችሁም፡፡ ፍጹም በሆነ ጨለማ ውስጥ ትሆናላችሁ፡፡ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ ይሆን?”
\v 24 “ለሁለት ጌቶች በአንዴ መገዛት የሚቻለው የለም፡፡ ወይ አንዱን ጠልቶ ሌላውኝ ይወዳል፤ አሊያም ለአንዱ ታማኝ ሆኖ ሌላውን ይክዳል፡፡ እንዲሁ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም፡፡”

2
06/25.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 25 ነው ለኑሮ ስለሚያስፈልጋችሁ ነገሮች ልትጨነቁ አይገባም ያልኋችሁ፡፡ በቂ የሆነ የምትበሉት ምግብ ኖራችሁ አልኖችሁ ወይም በቂ የምትለብሱት ልብስ ኖራችሁ አልኖራችሁ አትጨነቁ፡፡ ከእነዚህ ነገሮች ይልቅ አኗኗራችሁ ይበልጥ ዋጋ አለው፡፡
\v 26 እስኪ ስለ ወፎች አስቡ፡- ዘር አይዘሩም፣ ሰብልንም ወደ ጐተራ ሰብስበው አያስገቡም፡፡ የሰማዩ አባታችሁ ሁልጊዜ ምግባቸውን ያዛጋጅላቸዋል፡፡ እናንተ በእርግጥም ከወፎች ትበልጣላችሁ! ስለዚህም እግዚአብሔር የሚያስፈልጋችሁን እንደሚያዘጋጅላችሁ እርግጠኞች ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡

3
06/27.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 27 ከእናንተ በመጨነቅ ዕድሜውን ማሰረዘም የሚችል ማንም የለም፡፡ በሕይወታችሁ ላይ አንዲት ደቂቃን እንኳ መጨመር አትችሉም፡፡
\v 28 በቂ ልብስ የለኝም በሚለው ልትጨነቁ አይገባም፡፡ አበቦች የሚድጉበትን መንገድ እስኪ ተመልከቱ፡፡ ገንዘብን ለማግኘት አይሠሩም፥ የገዛ ራሳቸውን ልብስም አይሠሩም፡፡
\v 29 ዳሩ ግን ከብዙ ጊዜ በፊት የኖረው፣ እጅግ ውብ ልብሶች የነበረው ንጉሥ ሰሎሞን እንኳ እነዚህ አበቦች እንደ ለበሱት ያለውን ውብ ልብስ አለበሰም፡፡

2
06/30.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 30 እግዚአብሔር ዛሬ ታይተው ነገ የሚጠፉ የምድር አበቦችን እንዲህ አስውቧቸዋል፡፡ እናንተም ከሜዳ ከአበቦች ይልቅ ትበልጣላችሁ፡፡ እናንተ እምነት የጐደላችሁ! በእግዚአብሔር ታመኑ፡፡
\v 31 ስለዚህም ‹ምን እንበላለን? ወይም ‹ምን እንጠጣለን? ወይም ‹ምን እንለብሳለን? ብላችሁ ከቶ አትጨነቁ፡፡

3
06/32.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 32 እግዚአብሔርን የማያውቁ ሰዎች እንዲህ ባሉ ነገሮች ይጨነቃሉ፡፡ ዳሩ ግን በሰማይ ያለ አባታችሁ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል፡፡ ስለዚህም ልትጨነቊ አይገባችሁም፡፡
\v 33 ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት፥ ጽድቁንም ፈልጉ፡፡ ይህን ካደረጋችሁ፣ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ እግዚአብሔር ይሰጣኋል፡፡
\v 34 እንዲሁ ‘ነገ ምን ይከሰታል? ብላችሁ አትጨነቁ፥ ያም ቀን ሲመጣ ግድ የምትሰኙበት ብዙ ነገር ይኖራችኋል፡፡ ስለዚህ ስለ ነገ አትጨነቁ፡፡”

2
07/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\c 7 \v 1 “እንዳይፈረድባችሁ በማንም ላይ አትፍረዱ፡፡
\v 2 በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋል፡፡ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል፡፡”

3
07/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 4 \v 5 \v 3 “ማናችሁም ብትሆኑ ስለ ሌላው ጕድፍ ግድ ልትሰኙ አይገባችሁም፡፡ ይህም በሰው ዐይን ውስጥ ያለን ጕድፍ እንደ መመልከት ነው፡፡ ዳሩ ግን ስለ ራሳችሁ ትላልቅ ስሕተቶች ግድ ልትሰኙ ይገባል፡፡ እነዚህም ልክ በዐይኖቻችሁ እንዳሉና ልታዩዋቸው እንዳልቻላችኋቸው ያሉ ምስሶዎች ናቸው፡፡
4 ስለ ጥቃቅን ግድፈቱ ሌላውን “ጕድፍህን ከዐይንህ ላወጣልህ!” ልትሉ አይገባም፡፡ ምስሶው ገና በዐይናችሁ ውስጥ ሳለ ይህን ልትሉ አትችሉምና፡፡
5 እናንተ ግብዞች የገዘፉ ኃጢአቶችን መሥራት አቁሙ፡፡ ያን ጊዜም ትናንሽ ኃጢአቶችን የሚሠሩ ሰዎችን ማስቆም ትችላላችሁ፡፡”

1
07/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 6 “ተመልሰው እንዳይነክሷችሁ የእግዚአብሔርን ነገር ለውሾች አትስጡ፡፡ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ፥ ይረግጡዋቸዋልና፡፡ ይልቁንም በእናንተ ላይ ክፉ ነገርን ለሚያደርጉ ሰዎች የእግዚአብሔርን አስደናቂ ነገሮች አትንገሩዋቸው፡፡”

4
07/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,4 @@
\v 7 “የምትፈልጉትን እንዲሰጣችሁ እግዚአብሔርን ለምኑ፥ እንደሚሰጣቸሁም እመኑ፡፡
\v 8 እግዚአብሔር የሚጠይቀውንና እንደሚሰጠውም የሚያምን ሰው ይቀበላልና፡፡
\v 9 ልጁ እንጀራ ቢለምነው ከእናንተ ድንጋይ የሚሰጠው ማን አለ?
\v 10 ልጁ ዓሣ ቢለምነው ከእናንተ እባብ የሚሰጠው ማን አለ?

2
07/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 11 ክፉዎች ብትሆኑም ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ታውቃላችሁ፡፡ እንዲሁ በሰማይ ያለ አባታችሁ ለሚጠይቁት ይበልጥ መልካም ነገሮችን ይሰጣቸዋል፡፡”
\v 12 “እንግዲህ ሌሎች ሊያደርጉላቸው የምትሹትን ሁሉ፣ እንዲሁ እናንተ አድርጉላቸው፣ የእግዚአብሔር ሕግ ጸሐፊዎችና ነቢያት ከረጅም ዘመን በፊት የጻፉት ይህን ነውና፡፡”

1
07/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 13 \v 14 “ለዘላለም ከእግዚአብሔር ጋር ሊኖሩ መሄድ ከባድ ነው፥ ልክ ልትሄድበት እንደሚገባ መንገድ ያለ ነው፡፡ ብዙዎች የሚሄዱበት አንድ መንገድ አለ፡፡ ያም ሰፊ መንገድ ነው፡፡ ወደ ሰፊው በር እስኪደርሱ ይሄዳሉ፥ ዘልቀው በሄዱበት ጊዜም ይሞታሉ፡፡ ስለዚህም አስቸጋሪውን መንገድ እንድትሄዱ እነግራችኋለሁ፣ ደግሞም ከእግዚአብሔር ጋር በሰማይ ለዘላለም ትኖሩ ዘንድ በጠባቡ በር ግቡ፡፡”

3
07/15.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 15 “እግዚአብሔር እንዲህ አለ ብለው በሐሰት ከሚኖሩ ሰዎች ተጠንቀቊ፡፡ ጕዳት የማያስከትሉ ይመስላሉ፥ ዳሩ ግን ይህ ዕውነት አይደለም፡፡ የበግ ለምድ እንደ ለበሱ ተኵላዎች ናቸው፡፡ የማይጐዱ በጐች መሆናቸውን ሰዎች እንዲያምኑ ይፈልጋሉ፥ ዳሩ ግን እንደ ተኵላ ያጠቁዋቸኋል፡፡”
\v 16 “እንግዲህ ሐሰተኞች መሆናቸውን እንዴት ታውቃላችሁ? መልካም፣ የአንድን ተከል ፍሬ በማየት ምን እንደሆነ እንደሚታወቅ፣ እንዲሁ ምን ዐይነት ተክል እንደሆኑ ታውቃላችሁ፡፡ እሾህ የወይን ፍሬ ልያፈራ አይችልም፥ እንዲሁም ከእሾህ የወይን ፍሬ ስለ መልቀም የሚያስብ የለም፡፡ እንዲሁ ከኵርንችት በለስ አይለቀምም፡፡
\v 17 እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬን ይሰጣል፥ ክፉም ዛፍም እንዲሁ ክፉ ፍሬን ይሰጣል፡፡

3
07/18.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 18 መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬን እንደማይሰጥ፣ እንዲሁ ክፉ ዛፍም መልካም ፍሬን አይሰጥም፡፡
\v 19 መልካም ፍሬ የማይሰጥ ዛፍን ሁሉ ሠራተኞች ቈርጠው ያቃጥሉታል፡፡
\v 20 ከፍሬያቸው ምን እንደሆኑ ታውቃላችሁ፡፡ እንዲሁ ወደ እናንተ የሚመጡ ሰዎች የሚደርጉትን በመመልከት ስለ እግዚአብሔር የሚናገሩት ነገር ዕውነት መሆኑንና አለመሆኑን ታውቃላችሁ፡፡

3
07/21.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 21 ብዙዎች በልማድ ጌታ ሆይ ቢሉትም፣ የእርሱን ፈቃድ የማያደርጉ በመሆናቸው መንግሥተ ሰማይ አይገቡም፡፡ ፈቃዱን የሚያደርጉ ሰዎች ወደ መንግሥቱ እንዲገቡ አባቴ ይፈቅዳል፡፡
\v 22 እግዚአብሔር በሚፈርድበት ቀን ብዙዎች፣ “ጌታ ሆይ፥ ትንቢትን በስምህ አልተናገርንም ወይ? በስምህ ተአምራት አላደረግምን?” ይሉኛል፡፡
\v 23 እኔም በሁሉ ፊት፣ ‘እናንተ ክፉዎች፣ እኔ ከቶ የራሴ አድርጌ አልተቀበልኋችሁም’ እላቸዋለሁ፡፡”

2
07/24.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 24 “ስለዚህም የምለውን የሚሰማና የማዝዘውን የሚያደርግ፣ ቤቱን በዐለት ላይ እንደ ሠራ ብልህ ሰው ነው፡፡
\v 25 ዝናቡ ቢመጣም፣ ጐርፉም ቢጐርፍና ነፋሱ ቢነፍስም፥ ቤቱንም ቢመታውም እንኳ፣ በዐለት ላይ ስለ ተመሠረተ ቤቱ አልወደቀም፡፡

2
07/26.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 26 የምለውን የሚሰማና የማይታዘዘኝ፣ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል፡፡
\v 27 ዝናቡም በመጣ፣ ጐርፉም በጐረፈ፣ ነፋሱም በነፈሰና ቤቱን በመታው ጊዜ፣ በአሸዋ ላይ የተመሠረተ ስለ ነበረ ፈረሰ፥ ሙሉ በሙሉም ወደቀ፡፡ ስለዚህም ያዘዘኋችሁን ሁሉ ልትፈጽሙ ይገባችኋል፡፡

2
07/28.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 28 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አስተምሮ በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡
\v 29 እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ፣ ሌሎች ያስተማሩትን ትምህርት በመደጋገም እንደሚያስተምሩ እንደ ሕጉ መምህራን አልነበረም፡፡

3
08/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\c 8 \v 1 ከተራራም በወረደ ጊዜ ብዙዎች ተከተሉት፡፡
\v 2 ኢየሱስ ከሕዝቡ ጋር ከተለያየ በኋላ፣ እነሆ አንድ ለምጻም ወደ እርሱ መጥቶ በፊቱ ተንበረከከና “ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ ልታድነኝ እንደምትችል ዐውቃለሁና፣ እባክህ ፈውሰኝ” አለው፡፡
\v 3 ኢየሱስም ለምጻሞችን ከጤናማዎቹ ሰዎች የሚለየውን ሕግ አለፈውና ዕጆቹን ዘርግቶ ለምጻሙ ዳሰሰውና “እወዳለሁና፣ አሁን እፈውስሃለው አለው!” ወዲያውም ሰውየው ከለምጹ ነጻ፡፡

1
08/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 ኢየሱስም “በአቅራቢያው ወደሚገኝ ካህን ሂድና ራስህን አሳይ፡፡ እርሱም ለአካባቢው ሰዎች በነገራቸው ጊዜ፣ ከለምጽህ መንጻትህን ያረጋግጣሉ ደግሞም ከእነርሱ ጋር እንደገና ትቀላቀላለህ ከካህኑ በቀር እኔ እንደ ፈወስሁህ ለማንም አትንገር! ከዚያም ከለምጻቸው የተፈወሱ ሰዎች እንዲያቀርቡት ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ አቅርብ” አለው፡፡

3
08/05.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 5 ወደ ቅፍርናሆም በሄደ ጊዜ መቶ ወታደሮችን በሥሩ የሚያዝዝ የመቶ አለቃ ወደ እርሱ መጣ፥ እንዲረዳውም ኢየሱስን ለመነው፡፡
\v 6 እንደዚህም አለው፡- “ጌታ ሆይ፥ አገልጋዬ ታሞ በቤት የአልጋ ቁራኛ ሆኗል፥ ደግሞም በከባድ ሕመም እየተሰቃየ ነው፡፡”
\v 7 ኢየሱስም “ወደ ቤትህ ሄጄ እፈውሰዋለሁ!” አለው፡፡

3
08/08.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 8 የመቶ አለቃውም መልሶ “ወደዚያ ለመሄድ አትድከም! ከጣራዬ በታች እንድትገባና ከእኔ ጋር ቆይታ እንድታደርግ የሚገባኝ አይደለሁም፡፡
\v 9 እኔም እንደዚሁ ያሉ ገጠመኝ አለኝ፡፡ ወታደር ነኝና ለአዛዦቼ መታዘዝ ይኖርብኛል፡፡ ከእኔም በታች የማዝዛቸው ወታደሮች አሉ፡፡ አንዱን ሂድ ብለው ይሄዳል! ሌላውንም ና! ብለው ይመጣል፡፡ ለአገልጋዬም ‘ይህን አድርግ! ብለው ያደርጋል፡፡ አንተም እንደዚሁ በሥልጣን ማዘዝ ትችላለህ” አለ፡፡
\v 10 ኢየሱስም ይህን ሲሰማ ተደነቀ፡፡ ከእርሱ ጋር እየተጓዙ ላሉ ሰዎችም “ይህንን አድምጡ፡- ይህ ከአሕዛብ ወገን የሆነ ሰው ያለው ዐይነት እምነት በእስራኤል እንኳ ከቶ አላየሁም፡፡”

3
08/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 11 ዕውነት ዕውነት እላችኋለሁ፥ ብዙ ሰዎች ከምሥራቅ እና ከምዕራብ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፥ በእኔም ያምናሉ፥ በእግዚአብሔር መንግሥት ከአብርሃምና ከይስሐቅ፣ እንዲሁም ከያዕቆብ ጋር በአንድነት ይመገባሉ፡፡
\v 12 ዳሩ ግን የመንግሥት ልጆች እንዲሆኑ በእግዚአብሔር የተፈቀደላቸው አይሁድ ፍጹም የሆነ ጨለማ ወዳለበት ወደ ገሃነም ይጣላሉ፡፡ በዚያም ከስቃያቸው የተነሣ ያለቅሳሉ፥ ከስቃያቸው ክብደትም የተነሣ ጥርስ መፋጨት ይሆናል፡፡
\v 13 ከዚያም ኢየሱስ ለመቶ አለቃው “በሰላም ወደ ቤትህ ሂድ! እንደ እምነትህ ይሆንልሃል፡፡ ቃል ብቻ ብትናገር ብላቴናህ እንደሚፈወስ የተናገርኸው ይፈጸማል” አለው፡፡ መቶ አለቃውም ወደ ቤቱ ሄደ፥ አገልጋዩንም ኢየሱስ ይፈወሳል ባለው ጊዜም ተፈውሶ አገኘው፡፡

2
08/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 14 ኢየሱስም ከጥቂት ደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ጴጥሮስ ቤት ሄደ፥ የጴጥሮስ አማት በንዳድ ታምማ አልጋ ላይ ተኝታ አያት፡፡
\v 15 ዕጁንም ጫነባት፥ ወዲያውኑ ንዳዱ ለቀቃት፡፡ ተነሥታም በማዕድ አገለገለቻቸው፡፡

2
08/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 16 በዚያም ምሽት ሰንበት እንዳለፈ ሕዝቡ በርካታ በአጋንንት የተያዙ ሰዎችን፣ እንዲሁም የታመሙ ሌሎች ሰዎችን ወደ እርሱ አመጡ፡፡ እንዲወጡ በማዘዝም አጋንንቱን አስወጣቸው፥ በሽተኞቹንም ፈወሳቸው፡፡
\v 17 ይህንንም በማድረጉ በነቢዩ ኢሳይያስ “ሕዝቡን ከደዌያቸው ነጻ አደረጋቸው፥ እርሱም መልካም አደረገ” የተባለው ትንቢት ተፈጸመ፡፡

3
08/18.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 18 ኢየሱስም በዙሪያው የተሰበሰቡ ሰዎችን ተመለከተ፥ ነገር ግን ዕረፍት ማድረግን ፈለገ፡፡ ስለዚህም በታንኳ አድርገው ወደ ሌላኛው የባሕሩ አቅጣጫ እንዲወስዱት ደቀ መዛሙርቱን ተናገራቸው፡፡
\v 19 ወደ ታንኳ እየሄዱ ሳሉም አንድ ጻፊ ወደ እርሱ መጥቶ “መምህር ሆይ ወደምትሄድበት ሁሉ እሄዳለሁ!” አለው፡፡
\v 20 ኢየሱስም መልሶ “ለቀበሮዎች የሚኖሩበት ጒድጋድ፣ ወፎችም የሚያርፉበት ጎጆ አላቸው፣ ዳሩ ግን የሰው ልጅ ብሆንም መተኛት የምችልበት ቤት የለኝም!” አለው፡፡

2
08/21.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 21 ከኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አንዱም “ጌታ ሆይ አስቀድሜ ወደ ቤቴ እንድሄድና አባቴ ሲሞት እንድቀብረው፣ ከዚያም እንድከተልህ ፍቀድልኝ!” አለው፡፡
\v 22 ኢየሱስም “አሁኑኑ ተከተለኝ! እንደ ሟቾቹ ያሉት ሰዎች ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ተዋቸው” አለው፡፡

3
08/23.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 23 ከዚያም ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ታንኳው ገብተው መሄድ ጀመሩ፡፡
\v 24 ወዲያውም ማዕበል በባሕሩ ላይ ተነሣ፣ ታንኳይቱንም ውኃ እየሞላት ያናውጣት ጀመር፡፡ ኢየሱስ ግን ተኝቶ ነበር፡፡
\v 25 ሄደውም ቀሰቀሱትና “ጌታ ሆይ አድነን! ልንጠፋ ነውና!” አሉት፡፡

2
08/26.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 26 እርሱም፣ “ልትፈሩ አይገባም! ላድናችሁ እንደምችል ገና በእርግጠኝነት አላመናችሁም?” አላቸው፡፡ ተነሥቶም ነፋሱን ገሠጸው፥ ማዕበሉንም ጸጥ አደረገው፡፡ ወዲያውም ነፋሱ ዝም አለ፥ ማዕበሉም ጸጥ አለ፡፡
\v 27 ሰዎቹም ተደነቁ፣ እርስ በርሳቸው፣ “ይህ ሰው ከተለመደው የተለየ ነው፥ ሁሉም ነገሮች ይታዘዙለታል! ነፋሳትና ማዕበል እንኳ ይታዘዙለታል፡፡” ተባባሉ፡፡

2
08/28.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 28 ወደ ሐይቁ ምሥራቅ አቅጣጫ ሲመጡ፣ ወደ ጌርጌሴኖናውያን አገር ደረሱ፡፡ አጋንንት ያደሩባቸውን ሁለት ሰዎች ከመቃብር ወጥተው መጡ፡፡ እጅግ ኃይለኞችና ሰዎችን የሚያጠቁ ስለሆኑ፣ ማንም እነርሱ ወዳሉበት መንገድ ለመጓዝ አይደፍርም ነበር ፡፡
\v 29 “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ! ከእኛ ጋር ምን አለህ? ተወን! እግዚአብሔር ሊቀጣን ከመደበው ጊዜ በፊት ልታሰቃየን መጣህን?” እያሉ ጮኹ፡፡

3
08/30.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 30 ከዚያም ብዙ ሳይርቅ ይሰማራ የነበረ የእሪያዎች መንጋ ነበረ፡፡
\v 31 አጋንንቱም “ከእነዚህ ሰዎች ታወጣን እንደሆን፣ ወደ እነዚህ እሪያዎች ስደደን” እያሉ ኢየሱስን ለመኑት፡፡
\v 32 ኢየሱስም “ይህን ከፈለጋችሁ፣ ሂዱ!” አላቸው፡፡ አጋንንቱም ሰዎቹን ለቀው ወደ እሪያዎቹ ገቡ፡፡የእሪያዎቹ መንጋ ሁሉ እየተጣደፉ ወደ ባሕር ገብተው ሰጠሙ፡፡

2
08/33.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 33 እረኞቹም ፈሩ፥ ሮጠው ወደ ከተማ በመሄድም የሆነውን ሁሉ፣ አጋንንት ባደሩባቸው ሰዎችም የተደረግውን ነገር ሁሉ አወሩ፡፡
\v 34 ወዲያውኑም የከተማይቱ ሰዎች ሁሉ ኢየሱስን ሊገናኙ ሄዱ፡፡ ኢየሱስንና አጋንንትን አድረውባቸው የነበሩ ሁለቱ ሰዎችን ባዩ ጊዜ አገራቸውን ለቆ እንዲሄድ ለመኑት፡፡

2
09/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\c 9 \v 1 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ታንኳ ገቡ፡፡ በሐይቁም ላይ ተጕዘው ወደገዛ መኖሪያው ወደ ቅፍርናሆም ሄዱ፡፡
\v 2 ሰዎችም በአልጋ ላይ የተኛ ሽባን ወደ እርሱ አመጡ፡፡ ሽባውን ሰው እንደሚፈወስ ማመናቸውን ባየ ጊዜ “አንተ ልጅ፣ አይዞህ፣ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ!” አለው፡፡

4
09/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,4 @@
\v 3 ከጸሐፍትም አንዳንዶቹ “ይህ ሰው እግዚአብሔር እንደሆነ ያስባል፤ እርሱ ኃጢአትን ማስተሰረይ አይችልም!” በማለት እርስ በርሳቸው አጕተመተሙ፡፡
\v 4 የሚያስቡትን ያውቅ ነበር፥ ስለዚህም “ስለ እኔ ክፉ አሳቦችን ማውጠንጠን አይገባችሁም!” አላቸው፡፡
\v 5 “ኃጢአትህን ሰረይሁልህ!” ብሎ መናገር ለአንድ ሰው የሚከብድ አይደለም፥ ኃጢአቱ ይቅር መባሉንም ሆነ አለመባሉን የሚያይ የለምና፡፡ ዳሩ ግን “ተነሣና ተመላለስ!” ብሎ ሊናገር የሚደፍር ማንም የለም!
\v 6 የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ለማስተሰረይ ሥልጣን እንዳለው ታውቁ ዘንድ አንድ ነገር አደርጋለሁ አለ፡፡ ሽባውንም ሰው “ተነሣ! አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ!” አለው፡፡

3
09/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 7 ወዲያውም ሰውዬው ተነሣ፣ አልጋውን ተሸከመና ወደ ቤቱ ሄደ!
\v 8 ሕዝቡም ይህን በተመለከቱ ጊዜ ተደነቁ፡፡ እንዲህ ያለውን ተግባር ለመፈጸም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ እግዚአብሔርን አመስገኑት፡፡
\v 9 ኢየሱስም ከዚያ እየሄደ ሳለ ማቴዎስ የሚባልን ሰው ተመለከተ፡፡ ለሮማ መንግሥት ቀረጥ በሚሰበስብበት ሥፍራ ተቀምጦአል፡፡ ኢየሱስም “ወደ እኔ ናና ደቀ መዝሙሬ ሁን!” አለው፡፡ ማቴዎስም ተነሥቶ ከእርሱ ጋር ሄደ፡፡

2
09/10.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 10 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በማዕድ ተቀመጡ፡፡ እየበሉም ሳሉ ቀራጮችና የሙሴን ሕግ የሚጠብቁ ሰዎች መጥተው ከእነርሱ ጋር ተመገቡ፡፡
\v 11 ፊሪሳውያን ይህን በተመለከቱ ጊዜ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሄደው “መምህራችሁ ከቀራጮችና እነርሱን ከሚመስሉ ሰዎች ጋር መብላቱ ተገቢ አይደለም!” አሉዋቸው፡፡

2
09/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 12 ኢየሱስም የተናገሩትን ሰማና ይህን ምሳሌ ነገራቸው፡- “ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም፡፡”
\v 13 እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃላት ትርጓሜ ማወቅ አለባችሁ፡- “መሥዋዕትን ሳይሆን ምሕረትን እሻለሁ፡፡” ጻድቃን የሆኑ ሰዎችን ሳይሆን፣ ኃጢአተኞችን ከኃጢአታቸው ለመመለስ መምጣቴን ልብ በሉ፡፡

Some files were not shown because too many files have changed in this diff Show More