am_mal_text_ulb/04/01.txt

3 lines
753 B
Plaintext

\c 4 \v 1 “እብሪተኞችና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ ገለባ የሚሆኑበት እንደምድጃ እሳት የሚነድ ቀን ይመጣል። የሚመጣው ቀን ያነዳቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ፤ “ሥርም ሆን ቅርንጫፍ አይተውላቸውም።
\v 2 ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ ግን ፈውስ በክንፎቹ የያዘ የጽድቅ ፀሐይ ይወጣላቸዋል። እናንተም ከጋጥ እንደተለቀቁ እንቦሳ እየቦረቃችሁ ትወጣላችሁ።
\v 3 እኔ በምሠራበት ቀን ዐመፀኛውን ትረግጣላችሁ፤ ከእግራችሁ ጫማ በታች ዐመድ ይሆናሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።