\v 17 “እነርሱ የእኔ ይሆናሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ፣ “እኔ በምሠራበት ቀን ርስቴ ይሆናሉ። ለሚያገለግለው ልጁ እንደሚራራ ሰው እኔም እራራላቸዋለሁ። \v 18 በጻድቁና በዐመፀኛው መካከል፣ እግዚአብሔርን በሚያመልኩና እርሱን በማያመልኩ መካከል እንደገና ትለያላችሁ።