\v 6 እኔ ያህዌ አልተለወጥሁም፤ ስለዚህ እናንተ የያዕቆብ ልጆች አልጠፋችሁም።
\v 7 ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከትእዛዞቼ ፈቀቅ ብላችኋል፤ እነርሱንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ። እናንተ ግን፣ “የምንመለሰው እንዴት ነው?” ብላችኋል።