am_mal_text_ulb/02/14.txt

1 line
1.1 KiB
Plaintext

\v 14 እናንተም፣ “ይህ ለምን ሆነ?” በማለት ትጠይቃላችሁ። እንዲህ የሆነው ያህዌ በአንተና በወጣትነት ሚስትህ መካከል ምስክር ስለሆነ ነው፤ የቃል ኪዳን ጓደኝህና ሚስትህ ብትሆን እንኳ አንተ ለእርሷ ታማኝ አልነበርክም። \v 15 በመንፈሱ ክፋይ እግዚአብሔር አንድ አላደረጋቸውምን? እርሱ አንድ ያደረጋችሁ ለመንድነው? ምክንያቱም ለእግዚአብሔር የሚሆን መሥዋዕት ስለፈለገ ነው። ስለዚህ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤ ከወጣትነት ሚስታችሁ ጋር ያላችሁንም ታማኝነት አታጉድሉ። \v 16 “እኔ መፋታትን እጠላለሁ” ይላል የእስራኤል አምላክ ያህዌ፤ “ልብሱን በግፍ ሥራ የሚሸፍነውንውም ሰው እጠላለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ። “ስለዚህ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤ ታማኝነታችሁንም አታጉድሉ።”