\v 8 እናንተ ግን ከእውነተኛው መንገድ ወጥታችኋል። ሕጉን በተመለከተም ብዙዎችን አሰናክላችኋል፤ የሌዊን ኪዳን አፍርሳችኋል።” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ። \v 9 “መንገዴን አልጠበቃችሁም፤ ትምሕርቱን በተመለከተ አድልዎ አድርጋችኋል፤ ስለዚህ እኔም በሰዎች ሁሉ ፊት እንድትዋረዱና እንድትናቁ አደርጋለሁ።”