am_mal_text_ulb/02/05.txt

1 line
736 B
Plaintext

\v 5 “ከእርሱ ጋር ያደረግሁት ኪዳን የሕይወትና የሰላም ኪዳን ነበር፤ እነዚህን ለእርሱ ሰጠሁት፤ አከበርኩት፤ እርሱ አከበረኝ፤ በስሜ ፊት በፍርሃት በመንቀጥቀጥ ቆመ። \v 6 እውነተኛ ትምህርት በአንደበቱ ነበር፤ በከንፈሮቹ ምንም ሐሰት አልተገኘም። በሰላምና በጽድቅ ከእኔ ጋር ተመላለሰ፤ ብዙዎችንም ከኅጢአት መለሰ። \v 7 የካህኑ ከንፈሮች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ እርሱ የሠራዊት ጌታ የያህዌ መልዕክተኛ ስለሆነ ሰዎች ከአፉ ትምህርት መፈለግ ይኖርባቸዋል።