am_mal_text_ulb/01/13.txt

1 line
762 B
Plaintext

\v 13 ደግሞም፣ “ይህ ድካም ነው” በማለት ፣ “በንቀት ጢቅ አላችሁበት” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ። በዱር እንስሳ ተወስዶ የነበረውን ወይም አንካሳና በሽተኛውን መሥዋዕት ለማቅረብ ታመጣላችሁ። ታዲያ፣ ይህን ከእናንተ እጅ ልቀበል?” ይላል ያህዌ። \v 14 “መንጋው ውስጥ ያለውን ተባዕት በግ መሥዋዕት ለማቅረብ ተስሎ ሳለ ለእኔ ነውር ያለበትን እንስሳ የሚያቀርብ አታላይ ርጉም ይሁን! እኔ’ኮ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በአሕዛብ መካከል ይከበራል” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።