am_luk_text_ulb/15/17.txt

1 line
590 B
Plaintext

\v 17 እርሱም አንድ ቀን ወደ ልቡ ተመልሶ እንዲህ አለ፤ 'ምግብ የሚተርፋቸው የአባቴ ቤት ሠራተኞች ስንት ናቸው? \v 18 እኔ ግን እዚህ የምበላውን አጥቼ በራብ እሞታለሁ! ተነሥቼ ወደ አባቴ ቤት ልሂድና እንዲህ ልበለው፤ "አባቴ ሆይ፣ በእግዚአብሔርና በአንተ ፊት ኅጢአት አድርጌአለሁ። \v 19 ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ መጠራት አይገባኝም፤ ከአገልጋዮችህ እንደ አንዱ ቊጠረኝ።"