\v 10 ኢየሱስም በሰንበት ቀን በአንዱ ምኲራብ እያስተማረ ነበር። \v 11 ለዐሥራ ስምንት ዓመት ርኩስ መንፈስ ያጐበጣት አንዲት ሴት በዚያ ነበረች፡፡ እርስዋም ከመጒበጧ የተነሣ ቀና ብላ መቆም አትችልም ነበር፡፡