am_luk_text_ulb/03/15.txt

1 line
571 B
Plaintext

\v 15 ሕዝቡ የክርስቶስን መምጣት እየተጠባበቁ ሳሉ፣ ሰዎች ሁሉ በልባቸው እርሱ ክርስቶስ ይሆን እያሉ ስለ ዮሐንስ ይደነቁ ነበር፡፡ \v 16 እንደዚህ በማለት ዮሐንስ ለሁሉም መልስ ሰጣቸው፣ “እኔ በበኩሌ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፣ የጫማውን ማሠሪያ መፍታት እንኳን የማይገባኝ ከእኔ ይልቅ ብርቱ የሆነ ይመጣል፡፡ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፡፡