am_luk_text_ulb/02/36.txt

1 line
809 B
Plaintext

\v 36 ሐና የተባለች ነቢይትም በዚያ ነበረች፤ እርሷም ከአሴር ነገድ የሆነ የፋኑኤል ልጅ ነበረች፡፡ ዕድሜዋ እጅግ የገፋ ሲሆን ከጋብቻዋ በኋላ ከባልዋ ጋር ለሰባት ዓመታት ቆይታለች፡፡ \v 37 ከዚያ በኋላ ለሰማንያ አራት ዓመታት መበለት ሆና ኖራለች፡፡ ከቤተ መቅደስ በፍጹም ሳትለይ ቀንና ሌሊት በጾምና በጸሎት እግዚአብሔርን ታመልክ ነበር፡፡ \v 38 ልክ በዚያን ሰዓት ወደ እነርሱ መጥታ እግዚአብሔርን ማመስገን ጀመረች፡፡ የኢየሩሳሌምን መቤዠት ለሚጠባበቁ ለማንኛዎቹም ሰዎች ስለ ልጁ ትናገር ነበር፡፡