am_luk_text_ulb/10/13.txt

1 line
746 B
Plaintext

\v 13 ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተሳይዳ! በእናንተ ዘንድ የተደረጉት ታላላቅ ታምራቶች በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ የሐዘን ልብስ ለብሰውና ራሳቸውን አዋርደው ከረጅም ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበር፡፡ \v 14 ነገር ግን በፍርድ ወቅት ከእናንተ ይልቅ በጢሮስና በሲዶና ላይ የሚደርስባቸው ፍርድ የቀለለ ይሆናል፡፡ \v 15 እናንተስ በቅፍርናሆም ያላችሁት፣ እስከ ሰማይ ከፍ እንዳላችሁ ታስቡ ይሆን? እንደዚያ አታስቡ፣ እስከ ሲዖል ድረስ የምትወርዱ ትሆናላችሁ፡፡